ሼክ ኢብራሂም ቱፋ በኢራን ኤምባሲ በመገኘት ሀዘናቸውን ገለጹ

Date:

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼክ ኢብራሂም ቱፋ፣ የኢራን ከፍተኛ መሪን ህልፈት ተከትሎ በአዲስ አበባ በሚገኘው የኢራን ኤምባሲ በመገኘት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል።

ፕሬዝዳንቱ በኤምባሲው በተዘጋጀው የሀዘን መዝገብ ላይ በመፈረም፣ ለኢራን መንግስት እና ህዝብ ያላቸውን አጋርነት አረጋግጠዋል።

ሼክ ኢብራሂም በሰጡት መግለጫ፣ የተከሰተውን ክስተት “አሰቃቂ” ሲሉ የገለጹት ሲሆን፣ የመሪው ማረፍ ለኢራናውያን ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም ለሚገኙ ሙስሊሞች ሁሉ ታላቅ ኪሳራ መሆኑን በመልዕክታቸው አስፍረዋል።

የኢራን ኤምባሲ በበኩሉ የጠቅላይ ምክር ቤቱ መሪ በስፍራው ተገኝተው ላሳዩት አክብሮትና የሀዘን ተካፋይነት ያለውን ምስጋና አቅርቧል።

ይህ ጉብኝት በሁለቱ ሀገራት የሃይማኖት ተቋማትና ህዝቦች መካከል ያለውን ዲፕሎማሲያዊና መንፈሳዊ ትስስር የሚያጠናክር መሆኑም ተመላክቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...