በመቐለ ከተማ ከ17 ሺ ሊትር በላይ ነዳጅ በቁጥጥር ስር ዋለ

Date:

በመቐለ  ከተማ በሚገኙ 15 ነዳጅ ማደያዎች በቂ የነዳጅ አቅርቦት በማስገባት አገልግሎት እየተሰጠ የነበረ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ወደ ትግራይ ይገባ ነበረ ነዳጅ መቆራረጡን ተከትሎ በተፈጠረ የአቅርቦት ችግር ህገወጥ የነዳጅ ግብይትና ምርትን የመደበቅ ተግባራት መበራከታቸውን የመቐለ  ከተማ ምክትል ከንቲባ የሆኑ አቶ ኤልያስ ካህሳይ ገልፀዋል።

ምክትል ከንቲባው ይህን ተከትሎ በመቐለ  ከተማ አራት ክፍለ ከተሞች በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ 17 ሺ ሊትር በህገወጥ መንገድ የተከማቸ ነዳጅ በቁጥጥር ስር መዋሉን አስታውቀዋል።

ከዚህ ባሻገር የመሰረታዊ ሸቀጦች የዋጋ ንረት በከተማይቱ ስለመኖሩም በቅኝት ማረጋገጣቸው የገለፁት አቶ ኤልያስ ያልተገባ ትርፍን ለማግኘነት የሚሹ ነጋዴዎች የአቅርቦት እጥረት በሌለበት ሁኔታ በምግብ ዘይትና በሌሎች መሰረታዊ ሸቀጦች የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ መኖሩንና ይህንን አድርገው በተገኙ ነጋዴዎች ላይም የንግድ ተቋም እስከማሸግ የሚደርስ እርምጃ መወሰድ መጀመሩን መናገራቸዉን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በተመሳሳይ ሰው ሰራሽ የዋጋ ንረትና ምርትን በመደበቅ ስራ ተሰማርተው የተገኙ የአይደር፣ ዓዲ ሓቂ፣ ቀዳማይ ወያነና በኩሓ ክፍለ ከተማ በንግድ ስራ የተሰማሩ ስድስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸው የገለፁት ምክትል ከንቲባው ምርትን በመደበቅ የዋጋ ንረት እንዲፈጠር እያደረጉ ያሉትን ተከታትሎ በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ድንገተኛ ፍተሻዎቹ ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...