የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በወቅታዊ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ የተደረገውን የዋጋ ማስተካከያ ተከትሎ የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማሻሻያ አደረገ፡፡
አዲሱ የታሪፍ ማሻሻያ ከነገ መጋቢት 7 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን፥ ጭማሪው የከተማ አውቶብስ አገልግሎትን ጨምሮ በሚኒባስ፣ በሚዲባስና የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎችን ያካተተ ነው።
በመሆኑም የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ሁሉም ተቋማት፣ ባለንብረቶች፣ ማህበራትና ግለሰቦች በአገልጋይነት ስሜት ሕብረተሰቡን እንዲያገለግሉ ቢሮው ጠይቋል።
አገልግሎቱን በተገቢው መንገድ የማይሰጡና ሕብረተሰቡን ለተለያዩ እንግልቶችና ቢሮው ካስቀመጠው ህጋዊ ታሪፍ ውጪ የሚያስከፍሉ አገልግሎት ሰጪዎች ሲያጋጥሙ ሕብረተሰቡ ጥቆማ እንዲሰጥ ተጠይቋል።
በዚህም በነፃ የስልክ መስመር 9417 ወይም በአካል በአቅራቢያዎ በሚገኝ የትራንስፖርት ቅርጫፍ ጽሕፈት ቤቶችና የትራንስፖርት ዘርፍ ባለሙያች የተሽከርካሪውን ሰሌዳና ሰዓት በመያዝ ጥቆማ መስጠት እንደሚቻል የተቋሙ መረጃ አመልክቷል።
