በሜድትራንያን ባህር ላይ ከ3,500 በላይ ህፃናት መሞታቸውን ዩኒሴፍ አስታውቋል

Date:

ከ2015 ጀምሮ ወደ ጣሊያን ለመሻገር የሞከሩ 3500 ህፃናት መሞታቸውን ወይም የገቡበት አለመታወቁን ዩኒሴፍ አስታውቋል።

ከህፃናቱ በተጨማሪ 20,800 ሰዎች በተጠቀሰው አመት ውስጥ በባህሩ ላይ ህይወታቸውን እንዳጡ አስታውቋል።

ትክክለኛ ቁጥሩ ከዚህም ሊበልጥ እንደሚችል ያሳወቀው ዩኒሴፍ ሜድትራንያን ተሻግረው ጣሊያን ለመግባት ከሚሞክሩት መሃል 17% ያህሉ ህፃናት መሆናቸውንም ገልጿል።

ከህፃናቱ ውስጥ 70 በመቶዎች ለብቻቸው አስፈሪውን ጉዞ እንደሚያደርጉ የገለፀው ዩኒሴፍ ህፃናቱ ከጦርነት እና ከአስከፊ ድህነት ለመራቅ ጉዞውን እንደሚያደርጉ ገልጿል።

ዩኒሴፍ በየቀኑ በሜድትራንያን ባህር ላይ የአንድ ህፃን ህይወት ያልፋል ያለ ሲሆን ሁሉም አካላት የህፃናት እና የንፁሃን ዜጎች ደህንነት እንዲረጋገጥ እንዲሰሩ ጥሪውን አቅርቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...

የኢትዮጵያ አጠቃላይ ብድር 51.8 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ይፋ ሆኗል

ኢትዮጵያ  በድጋፍ መልክ ከአሜሪካ በየዓመቱ  በመንግስት በኩል ፈሰስ የሚደረግ...