በሰሜን አሜሪካ የሚካሄደው “ግራንድ አፍሪካን ራን” ከአጋሮቹ ጋር ተፈራረመ

Date:

ጊፍት ሪልስቴት እና አሪፍ ፔይ ከኖቫ ኮኔክሽንስ ኩባንያ ጋር ታላቁን የአፍሪካ ሩጫ እንደዚሁም የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድን በቀጣይ ዓመታት በአብሮነት ለማዘጋጀት ሰኔ 27/2017 ዓ.ም በአዲስአበባ በስካይላይት ሆቴል ስምምነት ፈፀሙ። ላለፉት ዓመታት በአጋርነት የቆየው አርትስ ቴሌቭዥንም በተመሳሳይ ስምምነት አከናውኗል።

በዕለቱም የግራንድ አፍሪካ ራን የ2025 የሩጫ ውድድር የመሮጫ ቲ-ሸርት በአምራቹ ጎፈሬ አማካይነት ይፋ ኾኗል።

“አብሮነት መሻል ነው” በሚል መሪ ቃል ቀጣዩ ውድድር በአመዛኙ ኢትዮጵያውያንንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ባሳተፈ መልኩ እኤአ ኦክቶበር 11 /2025 በዋሽንግተን ዲሲ የሚከናወን ሲኾን ኦክቶበር 12/2025 ደግሞ በመልካም ተግባራቸው ተፅዕኖ ለፈጠሩ ኢትዮጵያዊያን የዕውቅና መርሐግብር የሚሰጥበት አፍሪካን ኢምፓክት አዋርድ ይከናወናል።

በትላንቱ መርሐግብር ላይ የአፍሪካ ግራንድ ራን ቤተሰቦች፣ ታዋቂ አትሌቶች፣ አርቲስቶች፣ ጋዜጠኞች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የአፍሪካ ግራንድ ራን አጋሮች ዳሸን ባንክ፣ ጎፈሬ ስፖርት፣ አሌክሳንደሪያ ቶዮታ፣ ሮሚንግ ሮስተር፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን እንዲሁም አዳዲሶቹ አጋሮች ጊፍት ሪልስቴት፣ አሪፍ ፔይ በተወካዮቻቸው አማካይነት በአካልና በኢንተርኔት የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን ገልፀዋል።

ዶ/ር ጋሻው አብዛ፤ የግራንድ አፍሪካን ራን መሥራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ባለፉት ዓመታት አብረዋቸው ለተጓዙና ላገዟቸው ቤተሰቦች በሙሉ ላልተቋረጠ አጋርነታቸው ከፍ ያለ ምሥጋና አቅርበዋል።

ድሬቲዩብ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ

ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ዕድገት ወደር የሌለው አስተዋጽኦ ላበረከተውና የሙዚቃው...

ሕወሓት ድብረጺዮንን የክልሉ ፕሬዚዳንት አድርጎ መረጠ

የክልሉ ፕሬዚዳንት ተደርገው የተመረጡት  ድብርጺዮን ገ/ ሚካዔል (ዶ/ር)  ቃለ...

” ኢራን ከምድረ ገጽ ትጠፋለች ” – ትራምፕ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፎክስ ኒውስ ቴሌቪዥን ጋር ቃለ...

የአርበኞች ድል መታሰቢያ እና የዛሬው ትውልድ ለሕብረት ያለው አቋም

የጥንት ኢትዮጵያዊያንአርበኞች ድል 85 ኛው ዓመት መታሰቢያ ሚያዚያ...