የፊያታ አለም አቀፍ የአቅርቦት ሰንሰለት አስተዳደር ከፍተኛ ዲፕሎማ የአሰልጣኞች ስልጠና የማጠቃለያ መርሐግብር ማከናወኑን አስታወቀ።
በመርሃግብሩ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ ሚኒስትር ዶክተር አለሙ ስሜን ጨምሮ በርካታ የሃገር ዉስጥ እና አለም አቀፍ የሎጂስቲክ ባለሙያዎች ታድመዉበታል።
በተለያዩ የሙያ መስኮች ለተሰማሩ አርባ የሎጂስቲክ ባለሙያዎች ለአስራ አምስት ቀናት በፊያታ አለምአቀፋ ከፍተኛ ባለሙያ አማካኝነት የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጥቷል።
ሰልጠናዉ የኢትዮጵያ የሎጂስቲክስ ዘርፍ የሠዉ ሀይል ልማት ላይ የራሱን አሻራ እንደሚያሳርፍ እና የኢትዮጵያ የሎጂስቲክ ዘርፍ አንድ እርምጃ እንደሚያራምድ ተመላክቷል።
የኢትዮጵያ የእቃ አስተላፊዎችና የመረከብ ወኪሎች ማህበር ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ የሎጂስቲክ ዘርፍ በማዘመን ለአገሪቱ የምጣኔ ሃብት እድገት ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከተ ሲሆን በሎጂስቲክ ዘርፍ የሚታየውን ክፍተት ለመሙላት በርካታ እንቅስቃሴዎችን እንደሚያደርግም ተገልጿል።
