በባንኮች ላይ የ89 ሚሊዮን ብር ምዝበራ የፈጸመው ቡድን በቁጥጥር ሥር ዋለ

Date:



የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ባደረገው ክትትል፣ በሐሰተኛ የባንክ ዋስትና ሰነድ በመጠቀም

* በገዳ ባንክ፣
* በኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ እና
* በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ

ከባድ የሙስና ወንጀል የፈጸሙ ተጠርጣሪዎችን ከነግብረ-አበሮቻቸው በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታወቀ።

ተጠርጣሪዎቹ በተቀነባበረ ሴራ በአጠቃላይ ከ89 ሚሊዮን 296 ሺህ ብር በላይ በሀገር ኢኮኖሚ እና በባንኮች ላይ ጉዳት አድርሰዋል።

የጎደር ዋይን ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር ስራ አስኪያጅ ጌታሁን መለስ ሲሆን፣ ከገዳ ባንክ አገምሳ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አብዲሳ ቶሎሳ ጋር በጥቅም በመመሳጠር የቅርንጫፉን ፊርማና ማህተም ለወንጀል ተግባራቸው ሲጠቀሙበት ቆይተዋል።

ዋነኛው ተጠርጣሪ ጌታሁን መለስ ከዚህ ቀደምም በኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ላይ የ28 ሚሊዮን ብር እንዲሁም በንግድ ባንክ ላይ የ18 ሚሊዮን ብር የሐሰት ሰነድ ወንጀል ፈጽሞ ሲፈለግ የነበረ መሆኑ ታውቋል።

አበባው መኮንን የተባለ ሌላኛው ተጠርጣሪ ደግሞ ወንጀሉ እንዲፈጸም በማግባባትና ሁኔታዎችን በማመቻቸት ከፍተኛ የጥቅም ትስስር እንደነበረው ፖሊስ አረጋግጧል።

ፌደራል ፖሊስ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ አደጋ የሚደቅኑ ወንጀለኞችን የማደን ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል በመግለጽ፣ ህብረተሰቡ መሰል ህገወጥ ድርጊቶችን ሲመለከት በነፃ ስልክ መስመር 991 ወይም በ ‘EFPApp’ ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...