እሁድ ምሽት ኢራን ባስወነጨፈቻቸው ሚሳዔሎች በቴል አቪቭ በሚገኘው የኤምባሲያቸው ቅርንጫፍ “መጠነኛ ጉዳት” መድረሱን በእስራኤል የአሜሪካ አምባሳደር አስታወቁ።
ማይክ ሃካቢ በኤክስ ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት ቆንስላው “በኢራን ሚሳዔሎች ንዝረት” ጉዳት ስለደሰበት ዝግ ሆኖ ይቆያል ብለዋል።
የአሜሪካ ኤምባሲ በቴል አቪቭ እና በኢየሩሳሌም የሚገኙ ሠራተኞቹ መጠለያ ውስጥ እንዲቆዩ በትናንትናው ዕለት አሳስቦ ነበር።
በሚሳዔል ጥቃቱ የተጎዳ የኤምባሲው ሠራተኛ እንደሌለም አምባሳደሩ ተናግረዋል።
