በንጹኃን ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች በአስቸኳይ ይቁሙ

Date:

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) ሐሙሰ የካቲት 12 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁት ንጹኃን ሰዎች የተገደሉት በደቡብ ወሎ ዞን ወግዲ ወረዳ ጋሌ በተባለ ቦታ ጥር 26 ቀን 2018 ዓ.ም በመንግስት የጸጥታ አካላትና ታጣቂ ኃይሎች መካከል በነበረ የተኩስ ልውውጥ የተጎዳችን እንስት ወደ ሆስፒታል በሚወስዱበት ወቅት መሆኑን አመልክቷል፡፡

ማንነቷ በመግለጫው ያልተጠቀሰው ሴት እሷም የአካል ጉዳት የደረሰበት ከወንዝ ውሃ ቀድታ ስትመለስ በነበረበት ወቅት በሁለቱ ኃይሎች የተኩስ ልውውጥ በተባሪሪ ጥይት ቆስላ ነው፡፡ ከግድያና የአካል ጉዳት በተጨማሪ በሚተኮሱ ከባድ መሣሪያዎች ምክንያት የንብረት ውድመት መድረሱን ኢሰመጉ ከአካባቢው አሰባስቤያቸዋለሁ ካላቸው መረጃዎች ለማወቅ መቻሉን አስገንዝቧል፡፡

ኢሰመጉ የትናንቱ መግለጫው ሌላኛው ትኩረት ያደረገበት አካባቢ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ነው፡፡ በክልሉ የዘይሴ ማህበረሰብ ልዩ የወረዳነት መዋቅር ጥያቄ ጋር በተያያዘ ለረዥም ጊዜ በማህበረሰቡ ላይ የሞት፣ የአካል ጉዳት እና የንብረት ውድመት መድረሱንና አሁንም እየቀጠለ ያለ መሆኑን ኢሰመጉ አስታውቋል፡፡ ለዚህም አብነት ጠቅሷል፡፡

ግንቦት 4 ቀን 2017 ዓ.ም እና መስከረም 29 ቀን 2018 ዓ.ም አምስት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) አባላት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አድማ ብተና እና በጋሞ ዞን ፖሊሶች ተይዘው ይህ መግለጫ እስከተዘጋጀበት ጊዜ ድረስ የት እንዳሉ እንደማይታወቅ ገልጧል፡

በዘይሴ ዳንሌ ቀበሌ ልዩ ስሙ ቦሎዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ደግሞ በቀን ታህሳስ 05 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት በተወሰኑ በአካባቢው በሚኖሩ ሴቶች ላይ ጾታዊ ጥቃት መድረሱን፣  በቀጣዩ የጥር ወር በ19ኛው ቀን በዘይሴ ልዩ ምርጫ ክልል 4 አርሶ አደሮች በእርሻ ስራ ላይ እንዳሉ በክልሉ አድማ ብተናና በጋሞ ዞን ፖሊስ መገደላቸውን አጋልጧል፡፡

በተመሳሳይ ከየካቲት 8 10 ቀን 2018 ዓ.ም ባሉት ጊዜ ውስጥ የአካባቢው ነዋሪዎች ላይ በደረሰው ጥቃት ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች መገደላቸውን፣ የንብረት ውድመት እና መፈናቀል መድረሱን ኢሰመጉ ለማወቅ ችያለሁ ብሏል፡፡ ይሁንና የተጠቀሱትን ጉዳዮች በተመለከተ የመንግስትን ምላሽ ለማካተት ኢሰመጉ ከአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ አስተዳደር መረጃዎችን ለማግኘት አድርጌዋለሁ ያለው ጥረት እንዳልተሳከላት አመልክቷል፡፡

ሁለቱንም ክልሎች በተመለከተ ባስተላለፈው ጥሪ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የፍትህ አካላት በዘይሴ ዳንሌ ቀበሌ በሴቶች ላይ ጾታዊ ጥቃት የፈጸሙ የጸጥታ አካላትን ለፍርድ እንዲያቀርቡ፣  በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጸጥታ አካላት ተይዘው የት እንዳሉ የማይታወቁትን 5 የኢዜማ አባላትን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህና ጸጥታ አካላት የት እንዳሉ ለቤተሰቦቻቸው እንዲያሳውቁ እና በወንጀል የሚፈለጉ ከሆነ ወድያውኑ ለህግ በማቅረብ ፍትህ የማግኘት መብታቸውን እንዲያከብር ጠይቋል፡፡

የፌደራልና የአማራ ክልል መንግስታት በአማራ ክልል በንጹሀን ላይ እየደረሰ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት በቂ ትኩረት በመስጠት የሰዎች በህይወት የመኖር መብትን እንዲያከብሩና እንዲያስከብሩ ጥሪ አስተላልፏል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...