በአማራ ክልል 308 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሊገነቡ ነዉ

Date:

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር 308 ደረጃቸውን የጠበቁ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሊገነባ መሆኑን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ገልጿል ።

የቢሮዉ ኃላፊ አቶ ጥላሁን ወርቅነህ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት 154ቱ ትምህርት ቤቶች በፌደራል ትምህርት ሚኒስቴር በጀት ድጋፍ የሚገነቡ ሲሆን የተቀሩት 154 ደግሞ በወረዳና ህብረተሰቡ ተሳትፎ የሚገነቡ ናቸዉ ።

እነዚህም 308 ትምህርት ቤቶች በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ሁሉም ግንባታቸዉ ተጠናቆ ለ2019 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር አገልግሎት እንደሚሰጡ አቶ ጥላሁን ጨምረዉ ለጣቢያችን ተናግረዋል።

አሁን ላይ የተቋራጭ ልየታ ስራ እየተከናወነ መሆኑን የገለፁት ኃላፊዉ  የትምህርት ጥራት ችግርን በዘላቂነት ለመፍታትና ብቁና ተወዳዳሪ ዜጎችን ለመፍጠር ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ማስፋፋትና ማጠናከር ላይ በትኩረት እየተሰራ ነዉ ብለዋል ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...