በአረንጓዴ አሻራ ኢትዮጵያ ለዓለም የአየር ንብረት ለውጥ 48 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስት አድርጋለች

Date:

በአረንጓዴ አሻራ ኢትዮጵያ ለዓለም የአየር ንብርት ለውጥ 48 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስት አድርጋለች ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከምክር ቤት አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ማብራሪያ፤ በአረንጓዴ አሻራ ደረጃ ግብር 48 ቢሊዮን ችግኝ ተተክሏል፡፡

ይህም በአንድ ዶላር ቢሰላ ኢትዮጵያ ለዓለም አየር ንብርት ለውጥ 48 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስት አድርጋለች ለማለት ያስችላል ብለዋል፡፡

ይህም በዕርዳታና በድጋፍ ቢሆን የማይታሰብ ነበር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በመንግስትና በህዝብ የተገኘ ውጤት ነው ብለዋል፡፡

gazette_plus #ጋዜጣ_ፕላስ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ምንገድ ላይ

(በእውቀቱ ስዩም) በቀደም ከሆነ ቦታ ተነስቼ ወደ አልሆነ ቦታ ስራመድ...

ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ በጡረታ ከኃላፊነታቸው ተሰናበቱ

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያንና የአዲስ አበባ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ...

አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ አዲስ መግለጫ አወጣች

ታዋቂዋ አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ ለስፖርት ወዳጆችና ለደጋፊዎቿ ወቅታዊ መረጃ...