በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ አርሰናል እና ባርሴሎና ለፍጻሜ ደረሱ

Date:



በሴቶች የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታ አርሰናል ከሜዳው ውጭ ወደ ፈረንሳይ ተጉዞ ሊዮንን 4 ለ 1 አሸንፏል።

በሊዮን በተደረገው  ጨዋታ ማሪዮና ካልደንቲ ፣ አሊሲያ ሩቶ ፣  ኬትሊን ፎርድ እና ኢንድለር በራሷ መረብ ላይ የአርሰናልን ግቦች አስቆጥረዋል።

ዱሞናይ የሊዮንን አንድ ግብ ያስቆጠረች ተጫዋች ሆናለች።

በመጀመርያው ጨዋታ በሜዳው 2 ለ 1 ተሸንፎ የነበረው አርሰናል ውጤቱን ቀልብሶ በድምር ውጤት 5 ለ 3 በማሸነፍ  ከ18 አመት በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ የፍጻሜ ተፋላሚ መሆኑን አረጋግጧል።

በሌላ የግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታ ባርሴሎና ቼልሲን 4 ለ1 አሸንፏል።

በመጀመርያው ጨዋታም በተመሳሳይ 4 ለ 1 ያሸነፈው ባርሴሎና በድምር ውጤት 8 ለ 2 በማሸነፍ ለዋንጫ ጨዋታ ደርሷል።

በፍጻሜው አርሰናል ከባርሴሎና በሊዝበን የሚገናኙም ይሆናል።

በአንተነህ ሲሳይ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...