በአዲስ አበባ በጳጉሜን ወር የ45 የሀገራት መሪዎች ይሳተፋሉ

Date:

በአዲስ አበባ ከጳጉሜን 3 እስከ 5 ቀን 2017 ዓ.ም በሚካሄደው ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ የ45 የሀገራት መሪዎች እንደሚታደሙ ተገለጸ።

በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን በሚካሄደው ሁለተኛ የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ የአፍሪካ እና የአለም መሪዎች በጋራ ተገናኝተው ወደ ተግባር የሚለወጭ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ እንዲመክሩ ከማስቻሉም ባለፈ የተረጋገጡ አፍሪካዊ መፍትሄዎችን ለማሳየት የሚያስችል መድረክ ይፈጥራል ተብሏል።

ኢትዮጵያ በየክረምቶ በቢሊየኖች የሚቆጠር ችግኞች እየተተከሉ እንደሚገኝ በመጠቆም ከጳጉሜን 3 እስከ 5 ቀን በሚካሄደው ጉባኤው የአረንጓዴ አሻራ ትሩፋቶቿን ለማስተዋወቅ ትጠቀምበታለች ሲል የኬንያው ስታር ጋዜጣ በዘገባው ጠቁሟል።

በናይሮቢ ኬንያ ባሳለፍነው አመት 2016 ዓ.ም ጳጉሜን ወር ላይ በተካሄደው የመጀመሪያው የአፍሪካ አየር ንብረት ጉባኤ ላይ ሀገራት “የናይሮቢ ዲክላሬሽን” ስምምነትን ተቀብለው ማጽደቃቸው ይታወሳል።

“ይህ ስምምነት በዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ንግግር ለአፍሪካ የጋራ አቋም መሠረት ሆኖ ያገለግላል” ሲል የስምምነት ሰነዱ ያትታል።

የአፍሪካ ሀገራት “በሙሉ ድምጽ እና ድጋፍ” ተቀብለውታል የተባለው ይህ ስምምነት የአህጉሪቱ አቋም ሆኖ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚካሄዱ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ እና ኮንፈረንሶች ላይ የሚቀርብ ነው መባሉም በወቅቱ ተዘግቧል፡፡

ስምምነቱ የአየር ንብረትን ለመከላከል እና ለመቋቋም የአፍሪካ ሀገራት የሚተገብሯቸውን የፖሊሲ ማሻሻያዎች የያዘ እንዲሁም በኢኮኖሚ ያደጉ ሀገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ሊወስዷቸው የሚገቡ እርምጃዎችን ያስቀመጠ ነው፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...