“በአፋር የሚገኙ ታጣቂዎች ትንኮሳ የፌደራል ወይንም የአፋር ትንኮሳ አድርገን ነው የምንወስደው”

Date:

በአፋር ክልል የሚገኙ የትግራይ ታጣቂዎች የሚፈጽሙት ማንኛውም ትንኮሳ የፌደራል መንግስት ወይንም የአፋር ክልል መንግስት ትንኮሳ አደርገን ነው የምንወስደው ሲሉ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ ገለጹ።

የክልሉ የሰማዕታት ኮሚሽን ባዘጋጀው መድረክ ላይ ትላንት ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ “በዚያ በኩል የሚኖር ምንም አይነት ተነሳሽነት/እንቅስቃሴ እንደ ትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር፣ እዚያ ያሉ ሀይሎች ብቻ አድርጎ አይወስደውም፣ ወይ የፌደራል መንግስት ነው ካልሆነም የአፋር መንግስት ነው ብሎ ነው የሚወስደው” ብለዋል።

“እዛ ካሉት (ነጻ መሬት) ሀይሎች ጋር ያለው ልዩነት መቶ በመቶ መፈታት ያለበት በሰላማዊ መንገድ ነው፤ ነገር ግን ማንኛውም ትንኮሳ ከአፋር ክልል በኩል ከመጣ ወይ የአፋር መንገስት ነው አልያም የፌደራል መንግስቱ ነው ተብሎ የሚወሰድ እንጂ የትግራይ ተወላጆች /ተጋሩ ተደርጎ የሚወሰድ አይደለም” ሲሉም አስታውቀዋል፤ታጣቂዎች “የውክልና (Proxy) ሀይሎች ሁነው እንዳያገለግሉ የሚቻለንን ሁሉ እናደርጋለን ሲሉ መደመጣቸውንም ነው አዲስ ስታንዳርድ በዘገባው ያመላከተው፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ካናዳ ምዝገባም ሆነ ስምሪት አልተጀመረም

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መቀመጫውን ካናዳ ካደረገው "ፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል"...

የክቡር ዶክተር ጋሽ መሐሙድ አዲስ አልበም ለአድማጮች ሊደርስ ነዉ

ታዋቂው ድምፃዊ ክቡር ዶክተር አርቲስት መሐሙድ አሕመድ «ለታሪክ» የተሰኘውንና...

ሜታ ‘ፌስቡክ እና ኢንስታግራም በቀረበባቸው ክስ 18 ቢሊዮን ዶላር ለመክፈል ተስማማ

ግዙፉ የማኅበራዊ ሚዲያ ኩባንያ ሜታ በፌስቡክ እና በኢንስታግራም ምክንያት...