በኢትዮጵያ የአንድ ግራም የወርቅ ዋጋ ወደ 29 ሺህ ብር አሻቀበ

Date:

በኢትዮጵያ የ1 ግራም ወርቅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ በማሻቀብ ወደ 29,900 ብር መድረሱ ተነገረ። ካፒቲል ያደረገዉ የገበያ ቅኝት እንደሚያመለክተው፣ የአንድ ግራም ወርቅ ዋጋ በደረሰኝ (ከታክስ ጋር) ሲሰላ እስከ 29,900 ብር ደርሷል። የወርቁ ዋጋ ብቻዉን (ታክስ ሳይጨመር) ደግሞ 26,000 ብር ሆኗል።

በተመሳሳይ፣ አንዳንድ የሀገር ውስጥ ገበያ ዋጋዎች እንደሚጠቁሙት የወርቁ ዋጋ 25,000 ብር ሆኖ፣ ከእነ ደረሰኝ ሲሰላ ደግሞ 28,750 ብር መሆኑን ለመረዳት ተችሏል።

ይህ የወርቅ ዋጋ መጨመር በሀገር ውስጥ ያለውን የዋጋ ግሽበት እና ዓለም አቀፍ የወርቅ ገበያ መለዋወጥን የሚያመለክት እንደሚሆን ባለሞያዎች አስረድተዋል።

በተለይ የዋጋዉ መለዋወጥ የተስተዋለዉ ከሳምንታት በፊት ሲሆን ይህም በአንዱ የወርቅ ዋጋ ላይ ከ 2 ሺህ እስከ 3 ሺህ ብር ጭማሪ መደረጉን ካፒታል ሰምቷል።

የዚህ የዋጋው መናር በጌጣጌጥ ገበያ እና በወርቅ ተጠቃሚዎች ላይ ተጽዕኖ እንደሚፈጥር የሚናገሩት ባለሞያዎቹ አሁን የዚህ የዋጋ መለዋወጥ የሚቀጥል እንደሚሆን አፅንኦት በመስጠት ተናግረዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በመንገድ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ

አደጋው የደረሰው ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ...

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...