በእስር ላይ የሚገኙት መምህርት መስከረም ዓይናቸው በጽኑ መታመሙን ጠበቃቸው ገለጹ

Date:

ከሁለት ዓመት በላይ በእስር ላይ የሚገኙት መምህርት መስከረም አበራ “ ዓይናቸው በጽኑ መታመሙን ” ጠበቃቸው ሰለሞን ገዛኸኝ ነግረዋታል።

በእነ ዶክተር ወንደሰን አሰፋ መዝገብ ተከሳሾች መካከል አንደኛዋ የሆኑት መስከረም ከዚህ ቀደም ምንም ዓይነት ህመም ገጥሟቸው የማያውቅ መሆኑን ጠበቃቸው ያስታውሳሉ። ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዓይናቸው እጅጉን መታመሙን ጠቅሰዋል።

ይሁንና “ ካለፈው አንድ ወር ጀምሮ ዓይኗ ይቀላል፤ በጣም ስጋው ይታያል፤ ያማት ነበር፤ እንድትታከም ፍርድ ቤቱን ጠይቄ፣ ሄዳ ተመርምራ ነበር ” በማለት የጤና ክትትሉን አስታውሰዋል። በኋላም ሁለተኛ ምርመራ ማድረጋቸውን ያወሳሉ።

ጠበቃ ሰለሞን ከትናንት በስቲያ ሐሙስ ‛ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ’ በመሄድ መምህርቷን በአካል ያገኟቸዋል። ከዚህ ቀደም አንድ ዓይናቸውን ብቻ ቢሆንም ሲያገኟት ግን ሁለቱም መታመማቸውን ይመለከታሉ።

“ሁለቱም ዓይኖቿ ታምመዋል፤ ከፍተኛ ስቃይ ውስጥ ነው ያለችው ” ያሉት ሰለሞን ከዚያም ትናንት ዓርብ በአስቸኳይ ፍርድ ቤት ይሄዳሉ።

“ የፍርድ ቤቱ የመሃል ዳኛም ያለምንም ማወላወል፣ በፍጥነት ትታከም የሚል ትዕዛዝ ሰጥተው ነበር፤ ነገር ግን የትዕዛዙ ወረቀት ሳይወጣ ቀርቷል ” ብለዋል።

እናም ቅዳሜ፣ ዛሬም እሁድ፣ ሰኞም በዓል በመሆኑ መምህርት መስከረም አስቸኳይ ህክምና የማግኘታቸው ነገር አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱን አመልክተዋል።

መምህርቷ ግን በጽኑ መታመማቸውን አጽዕኖት ሰጥተዋል።

(አዲስ ማለዳ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ10 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ጥቅምት 12 ቀን 2019...

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ የፕላቲንየም ብራንድ የማስተር ካርድ ይፋ አደረጉ

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ደንበኞች የፕሪሚየም...

የአሜሪካ የደህንነት ኃላፊ ኢራንን አስጠነቀቁ

ቡሔራዊ ደህንነት ዳይሬክተር ጄይ ክላይተን አርብ ዕለት ኢራን በውጭ...

ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ  በአመት ከ1.1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ታጣለች

85 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ በግብርናው ዘርፍ የተሰማራ ሲሆን...