እስራኤል በጋዛ አጠናክራ በቀጠለችው ጥቃት የሃማስ ቃል አቀባይ አብደል ላቲፍ አል ቃኑዋ ህይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል፡፡
ቃል አቀባዩ የእስራኤል ተዋጊ ጄቶች በሰሜናዊቷ ጃባሊያ መጠለያ ባደረሱት የቦምብ ጥቃት መሞታቸው ነው የተገለፀው፡፡
በጥቃቱ ህፃናት ጨምሮ በርካታ ሰዎች ሲቆስሉ በአንድ መኖሪያ ቤት በተፈፀመ ጥቃት ስድስት የአንድ ቤተሰብ አባላት ህይወታቸው አልፏል፡፡
ባለፈው ሳምንት በርካታ የሃማስ ከፍተኛ ባለስልጣናት በእስራኤል ጥቃት ህይወታቸው ማለፉ ይታወቃል፡፡
ዘገባው የአልጀዚራ ነው
