በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ የተንሰራፋውን  ሙስና

Date:



በዘርፉ ላይ ያለውን የ #ሙስና ችግር ለመፍታት ይረዳል የተባለው እና እስከ 2030 ዓ.ም የሚያገለግል የኮንስትራክሽን ፖሊሲ ጸድቋል፡፡

ነባሩ ማለትም በ2006 ዓ.ም የወጣው እና ለለፉት 11 ዓመታት ያገለገው ፖሊሲ በርካታ ከፍተቶች እንደነበሩት ተጠቅሷል፡፡

ካሉበት ችግሮች መካከል የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪው ውቅር በአመዛኙ በጥርጣሬ ላይ የተመሰረተ እንዲሆን አድርጓል ይላል ሰነዱ፡፡

ለመልካም አፈጻጸም ማበረታቻ የሚሰጥበት ፤ የሚጠበቅባቸውን ኃሊፊነት በአግባቡ ባልተወጡ አካላት ሊይ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የሚስችል አሰራር እንዳልነበረው የተጠቀሰ ሲሆን የአገር ውስጥ ተቋራጮች እና አማካሪ ድርጅቶች የፋይናንስ አቅማቸው ጠንካራ እንዳይሆኑ አድርጓል ብሏል፡፡

እነዚህም ለፖሊሲው መሻሻል ከተዘረዘሩ ምክንያቶች መካከል ናቸው፡፡

በተጨማሪም የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች ተወዳዳሪ እንዲሆኑ፣ ከውጭ ሀገር ኩባንያዎች ጋር በሽርክና /Joint Venture/ ተጣምረው ሊሰሩ የሚችሉበት ግልፅ የአሠራር ሥርዓት አለመዘርጋቱ እና በመንግስት እና በግለ ዘርፍ ሙስናና ብልሹ አሠራር መንሰራፋቱ ለፖሊሲው መሻሻል በምክንያትነት ተጠቅሰዋል፡፡

የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪው ለኢኮኖሚው ባላው ፋይዲ ልክ ተወዳዳሪ መሆን አለማቻሉ፣ዘርፉ ከውጭ በሚገቡ የግንባታ ግብአቶች ላይ ጥገኛ በመሆኑ የሀገር ውስጥ ተኪ ግብዓት አምራቾችን ሊፈጥርና ሉያነቃቃ አለመቻሉ ተጨማሪ ምክንያት ነው ይልል፡፡

ፕሮጀክቶች በተቀመጠላቸው ዋጋ፣ የማጠናቀቂያ ጊዛ እና የጥራት ደረጃ እንዱከናወኑ ማስቻል፣የአገር በቀል የኮንስትራክሽን ኩባንያዎች በሰው ሃይል ብቃት፣ በሥነ-ምግባር ብቁ ማድረግ ፣የመንግስትና የግል አጋርነትን ማጠናከር እና የፋይናንስ ችግርን መፍታት ከፖሊሲው ዓላመዎች መካካል ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

በ2030 ዓ.ም የኢትዮጵያን ብልፅግና በአስተማማኝ ሁኔታ የሚደግፍ እና በቀጣናው ተወዳዳሪ የሆነ የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪን እውን ማድረግ ደግሞ የፖሊሲው ራዕይ ሆኖ ተጠቅሷል፡፡

የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪው ተወዳዳሪነት እና ፍላጎት ጋር አብሮ የሚሄድ እንዲሆን ዘርፉ የሚፈልገው የሰው ኃይል፣ እውቀትና ክህልት እንዲያድግ ፣ዘመናዊ የኮንስትራክሽን ፍቃድ አሰጣጥ ሥርዓት እንዲኖር ይደረጋል፣ጠንካራ የኮንስትራክሽን ኮንትራት አስተዳደር ሥርዓት ይዘረጋል እንዲሁም ዘርፉ የሚመራበት የህግ ማእቀፍ ይዘጋጃል ይልል ፖሊሲው፡፡

የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪው አማራጭ የካፒታል ፋይናንስ ምንጭ እንዲኖረው ደግሞ ተቋራጮች እና ለኮንስትራክሽን ማሽነሪ አከራዮች የመሳሪያ ግዥ የሚውል የብድር አቅርቦት ሥርዓት ይዘረጋል፣የግል ሴክተር በመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ላይ ከመንግስት ጋር በቅንጅት የሚሰራበት  ሥርዓት ይኖራል እንዲሁም በኮንስትራክሽን ግብአቶች አቅርቦትና የግንባታ እቃዎች ላይ የዋጋ ግሽበት መቆጣጠሪያ  ሥርዓት እንደሚዘረጋ ተነግሯል፡፡

ለዘርፉ ስነ ምግባር ደግሞ የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪው ተሳታፊ አካላት የሚመሩበት ወጥ እና አስገዳጅ የሆነ የኮንስትራክሽን ሥነ-ምግባር ደንብ ተዘጋጅቶ እንደሚተገበር፣የኮንስትራከሽን ኢንደስትሪው ተዋናዮች የምዝባና የብቃት ማረጋገጫ አሰጣጥ የሥነ ምግባር ቅድመ ሁኔታ እንዲያሟሉም ይደረጋል፡፡

ፖሊሲውን ለማስፈጸም ደግሞ የ14 ተቋማት ተዘርዝረዋል፡፡

በዚህም መሰረት የከተማና መሠረት ልማት ፣ኢንደስትሪ ፣የንግዴና ቀጣናዊ ትስስር፣የማዕዴን፣የሥራና ክህልት፣የገንዘብ፣የገቢዎች፣የፕሊንና ልማት፣የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ፣የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ፣የውሀና ኢነርጂ፣የትምህርት ሚኒስቴር እንዲሁም የፖሊሲ ጥናት ኢንስትቲዩት ተቋም ተዘርዝረዋል፡፡

የስራ መስኩ  ከግብርናው ዘርፍ በመቀጠል ከፍተኛ የኢኮኖሚ ሚና ድርሻ አለው የተባለ ሲሆን  ወደ 20 በመቶ የሚጠጋውን አጠቃሊይ የሀገር ውስጥ ጥቅል ምርት ተብሏል፡፡

በተጨማሪም  እስከ 10 በመቶ ለሚሆነውን አምራች የማህበረሰብ ክፍል የሥራ ዕድልን የሚፈጥር መሆኑ ተነግሯል፡፡

ሸገር 102.1

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ከፖለቲካ ራሳቸውን አገለሉ

ላለፉት 5 አስቸጋሪና ፈታኝ ዓመታት (ከ2014 እስከ 2018 ዓ.ም)...

ንባብ ለሕይወት  እየመጣ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

“ወጣቱን በጉልበት እያፈሱ ወደ ጦርነት እየነዱት ነው!”

"ሰላም፣ ዴሞክራሲና ልማት በትግራይ፦ የመገናኛ ብዙኃን እና የማኅበረሰብ አንቂዎች...