በዩክሬን ጦርነት ላይ የመከረው የአላስካው ስብሰባ

Date:


የፕሬዝዳንት ትራምፕና ፕሬዝዳንት ፑቲን የአላስካ ውይይት በሩሲያና ዩክሬን የተኩስ ማቆም ላይ ከስምምነት ሳይደርሱ መቋጨቱን ሁለቱ መሪዎች አስታውቀዋል።ፑቲን ጦርነቱን ለማስቆምና ሰላም ለማምጣት የችግሩን መነሻ ክስር መሰረቱ መረዳት ያስፈልጋል ሲሉ፤ ትራም በበኩላቸው“በጣም ፍሬያማ ውይይት አካሂደናል፤ሆኖም ግን በዋናው ጉዳይ ላይ ገና ነን” ብለዋል።

 አውርፓን አስጭንቆ ዩክሬንን አስግቶ የቆየው የፕሬዝዳንት ትራምፕና ፕሬዝዳንት ፑቲን የአላስካ ውይይት በሩሲያና ዩክሬን የተኩስ ማቆም ላይ ከስምምነት ሳይደርሱ የተቋጨ መሆኑን ሁለቱ መሪዎች ዛሬ ንጋት ላይ በጋራ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

ሁለቱ መሪዎች በዩክሬን ጦርነት ላይ፤ ግን እራሷን ዩክሬንና አውሮፓን ስያካትቱ ለመጋገር መወሰናቸው ነበር፤ ዩክሬንንና አውሮፓን ሲበዛ ስጭንቆ  የስነበተው። ለሩሲያ ያደላ፤የዩክሬንን ለኡላዊነት የሚጻረርና ያውሮፓንም ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል ስምምነት ላይ እንዳይደርሱ፤  ፕሬዝዳንት ትራምፕን የአውርፓ መሪዎች በግልም በቡድናም ሲያሳስቡና ሲማጸኑ ነው የከረሙት።  


የስብሰባው ውጤት 


ሁለቱም መሪዎች ስብሰባው ይወስዳል ከተባለው ሰአት ባነሰ ግዜ ወጥተው በሰጡት መገልጫ፤  ስብሰባው  በጥሩ ሁኔታ የተካሄደ  ቢሆንም፤ ጦርነቱን ለማስቆም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ  ግን ለግዜው ለመስማማት ያልተቻለ መሆኑን ገልጸዋል።

ፕሬዝዳንት ፑቲን ስብሰባውን ጦርነቱን ለማስቆምና ሰላም ለመፍጠር የችግሩን ምክኒያት ክስር መሰረቱ መረዳት እንደሚያስፈልግ አጽናኦት ሲሰጡ፤ ፕሬዝዳንት ትራም በበኩላቸው “በጣም ፍሬያማ  ውይይት አካሂደናል፤ በበርካታ ጉዳዮች ላይም ክስምምነት ደርሰናል፤ ሆኖም ግን በዋናው ጉዳይ ላይ ገና ነን” በማለት የተኩስ ማቆም ስምምነት ላይ ለመድረስ ያልተቻለ መሆኑን አስታውቀዋል።


በስብሰባው ውጤት  ላይ የሚሰጡ አስተያየቶች


የስብሰባው ውጤትና የመሪዎቹ መግለጫ  በአንድንዶች የተጠበቀ ሲሆን በሌሎች፤ በተለይም ፕሬዝዳንት ትራምፕ ጦርነቱን እንደሚያስቆሙሲፎክሩ ከነበረው አንጻር የተጠብቀ አልነበረም።

ሆኖም ግን የአውርፓና የስሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት መሪዎች፤ መጥፎ ስምምነት ላይ ከሚደረስ ምንም አይነት ስምምነት ላይ ባይደረስ  ይመርጡ እንነበር  ነው ታዛቢዎች የሚናገሩት።


የአውሮፓ መሪዎች ምስጋናና ማሳሰቢያ


ፕሬዝዳንት ራምፕ የስብሰባውን ውጤት ላውርፓና የኩሬንን መሪዎች ማለዳ በስልክ ያሳወቁ ሲሆን፤የአውርፓ መሪዎች በተለይም ፕሬዝዳንት ማክሮ፣ ቻንስለር ሜርዝ፣ ጠቅላይ ሚኒሰትር ስታርመር፣ ጠቅላይ ሚኒስተር ሜሎኒንና ያውሮፓ ህብረት ተቋማት ፕሬዝዳነቶች ዛሬ በጋራ ባወጡት መግለጫ፤  ፕሬዝዳንት ትራምፕን ለጥረታቸው አመስግነው፤ የሚቀጥለው እርምጃ ፕሬዝዳንት ዜለንስኪ  የሚሳተፉበት ስብሰባ መጥራት ሌሆን እንደሚገባው  አሳስበዋል።፡


 ትርፍና ኪሳራ


ይህ ስብሰባ አሁን በተጨባጭ የዩኪረንን ጦርነት ባያስቆምም ለቀጣይ ስብሰባ መነሻ ሊሆን እንደሚችል ግን በብዙዎች ይታመናል። ቀደሞ በተባበሩትመንግስታታት ድርጅት የአሜሪካ  አምባሰደር የነበሩት ሚስተር ጆን ቦልቶን፤ በዚህም ቢሆን  ያተረፈም የከሰረም ያለ መሆኑን ሲገለልፁ  “ እንደሚመሰልኝ ትራምፕ አልከሰሩም ግን ፑቲን በግልጽ በዚህ አሸናፊ ሆነው ወተዋል፤ የሚፍለግቱንም ያገኙ ይመስለኛል ብለዋል።

dw Amharic

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሴቶችን በቤት ውስጥ በማገዝ  መልካም ማህበረሰብ መፍጠር ተጀምሯል

በቤት ውስጥ የሚሠሩ ተግባራትን ተከፋፍሎ በመሥራት ሴቶችና እናቶችን መደገፍ...

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...