ድል አስጎብኚና የጉዞ ወኪል ገጣሚ ምሥራቅ ተረፈን የብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾመ

Date:

ድል አስጎብኘና የጉዞ ወኪል በዓለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት ማህበር የተመዘገበና የተፈቀደለት የትራቭል ኤጀንት (IATA ACCREDITED AGENT) ሲሆን በቱሪዝም ዘርፍ በቂ ትምህርትና ልምድ ያላቸውን የበረራ ትኬት ሽያጭና የቱር ኦፕሬሽን ባለሙያዎችን ያቀፈ ድርጅት ነው።

በሁሉም አየር መንገዶች የበረራ ትኬቶች፣ ወደ ተለያዩ ሃገራት ለሚያደርጉት ጉዞዎች የሆቴል ሪዘርቬሽን በተመጣጣኝ ዋጋ፣ የመንፈሳዊና የእረፍት ጊዜ የጉብኝት ፓኬጆች፣ የቪዛ ማመልከቻ ሂደት እገዛና የምክር አገልግሎት፣ ጨምሮ አጠቃላይ የጉዞ የምክር አገልግሎት በመስጠት ይታወቃል።

ባለፉት ጥቂት ዓመታትም ከቅድስት ሃገር ኢየሩሳሌም መንፈሳዊ ጉብኝቶች፣ በበርካታ አውሮፓ ሃገራት፣ በመካከለኛው ምስራቅ ዱባይ፣ ቱርክ፣ በሩቅ ምስራቅ ሃገራት ታይላንድና ጃፓን፣ በላቲን አሜሪካ ብራዚልና አርጀንቲና፣ በፈር ቀዳጅነትና በስኬት ካካሄዳቸው የዓለ ዓቀፍ የቡድን የጉብኝት ፕሮግራሞች ውስጥ ተጠቃሾቹ ናቸው።

የቅድስት ሃገር ኢየሩሳሌም መንፈሳዊ ጉብኝት በየአመቱ ለመስቀል፣ ለልደት/ለገና፣ ለደብረዘይት፣ ለትንሳዔ፣ ለዕርገት እና ለፍለሰታ በዓላት ጉዞዎችን በስኬት ያቀዳጀ መሆኑ በስፋት ይነገርለታል፡፡

ድል አስጎብኚና የጉዞ ወኪል ጦቢያ ” ግጥምን በጃዝ” በሚባል የሚታወቀውንና በሀገር ብቻ ሳይሆን በውጪ ሃገራትም ከፍተኛ ዕውቅና እና ክብር ያተረፈውን ዝግጅት ዋና አዘጋጅ ገጣሚ ምሥራቅ ተረፈን ያላትን ተወዳጅነት እና ታማኝነት በማየት ለብራንድ አምባሳደርነት በሙሉ እምነት መምረጡን የአስጎብኚና የጉዞ ወኪሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ድልነሳሁ ዓለሙ ገልፀዋል።

በካዛንቺስ ከግቢ ገብርኤል መግቢያ በግራንድ ፖላስ ፓርኪንግ ህንፃ 1ኛ ፎቅ መቀመጫውን ያደረገው ድል አስጎብኚና የጉዞ ወኪል ለቀጣይ አንድ ዓመት ያህል ወደ ቅድስት ሃገር ኢየሩሳሌም አምስት ጉዞዎችን ለማድረግ ዝግጅቱን ያጠናቀቀ ሲሆን ለዚህም የተሳካ የስራ ዘመን ይሆን ዘንድ የድርጅቱን ብራንድ አምባሳደር ገጣሚ ምሥራቅ ተረፈን፣ ዛሬ ሚያዚያ 15 ቀን 2017 ዓ.ም በግል ቢሮው በተካሄደ ልዩ ስነ-ስርዓት የክብር አምባሳደር አድርጎ በክብር ሸሟታል።

የድል አስጎብኚና የጉዞ ወኪል ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ድልነሳሁ ዓለሙ እንደተናገሩት “ገጣሚ ምሥራቅ ተረፈን” የመረጥንበት ምክንያት በኪነጥበብ ዘርፍ ላይ ስኬታማና ማህበረስብ ተወዳጅነትና ታአማኒነት እንዲሁም በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በውጪ ሃገራትም ያላትን ድንቅ ዕውቅናና ተወዳጅነት በማገናዘብ የድል አስጎብኚና የጉዞ ወኪል ቀጣይ የሥራ ጉዞን ለማሳካት ትክክለኛ ምርጫ ናት ብለን በማመናችን በክብር መርጠናታል” ብለዋል።

ገጣሚ ምሥራቅ ተረፈም በበኩሏ “ለእንደዚህ ያለ ስኬታማና ተአማኒነትን ያተረፈ ድርጅት ብራንድ አምባሳደር በመሆኗ የተሰማትን ደስታ ገልፃ ይህንን ኃላፊነት እንደምወጣ አምኖብኝ የመረጠኝን የድል አስጎብኚና የጉዞ ወኪል እያመሠገንኩ፥ በሚጠበቅብኝ አቅምና ብቃት ለማስተዋወቅ ድርጅቱ ያቀረበልኝን የአብረን እንስራ ጥሪ በደስታ ተቀብያለሁ።” በማለት ተናግራለች፡፡

ድል አስጎብኚና የጉዞ ወኪል በቀጣይም የጌታችን የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን የእርገት በዓልን ምከንያት በማድረግ ወደ ቅድስት ሃገር ኢየሩሳሌም ጉዞ ለማድረግ ዝግጅቱን አጠናቆ በቀሩት ጥቂት ቦታዎች ምዝገባ እያደረገ መሆኑን አያይዞ አሳውቋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...