በጋምቤላ ብቻ የሚገኘው የሺአ ቅቤ (ሺአ በተር) ዛፍ ሽፋን እየቀነሰ መምጣቱ ተነገረ

Date:

በጋምቤላ ክልል ብቻ የሚገኘው የ’ሺአ ቅቤ’ ዛፍ (shea butter tree) ትኩረት ከተሠጠው ከምዕራብ አፍሪካ የሚገባውን ምርት ከማስቀረት ባለፈ የውጭ ምንዛሬ ማስገኘት የሚችል ቢሆንም፤ በአሁኑ ጊዜ የዛፉ ሽፋን እየቀነሰ መምጣቱ ተነግሯል።

በክልሉ አራት ወረዳዎችን የሚያካልለው የ’ሺአ በተር’ ዛፍ በምስራቅ አፍሪካ የሚገኘው የዝርያ አይነት እንደሆነ በዘርፉ ከ13 ዓመታት በላይ የሰሩትና በአሁኑ ወቅት በሜርሲኮፕ ኢትዮጵያ የጋምቤላ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ስመኘው ታደሰ ለአሐዱ ተናግረዋል። 

ዛፉ በምዕራብ አፍሪካ ከሚገኘው ዝርያ ጋር ሲወዳደር ለየት ያለ እና ተመራጭ ቢሆንም፤ ትኩረት እንዳልተሰጠው ሥራ አስኪያጁ ገልጸዋል።

“በተለይም በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ የሺአ በተርን ዛፍ ከጋና ታስመጣለች” ያሉት ሥራ አስኪያጁ፤ እንደ ቅባት እና ሎሽን አይነት ምርቶች የሚገኙት ከሺያ በተር እንደሆነ አብራርተዋል።

ዛፉ ፍሬ ለመስጠት ከ15 እስከ 20 ዓመት ጊዜ እንደሚወስድ እና ከ100 ዓመት በላይ እድሜ እንደሚኖርም አንስተዋል።

“የአካባቢው ሰዎች በባህላዊ መንገድ አዘጋጅተው እየተጠቀሙበት ቢሆንም፤ በጣም አድካሚ በመሆኑ እየተውት መጥተዋል” ብለዋል።

ዛፉ ከኮልስትሮል ነፃ እና የማያስረጅ በመሆኑ ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው የሚያነሱት ሥራ አስኪያጁ፤ ሀብቱ ተጠብቆ በደንብ ቢሰራበት እንዲሁም እሴት ቢጨመርበት ለአካባቢውም ለሀገርም ጠቀሜታ እንዳለው አስረድተዋል።

እንደ ተግዳሮት የሚነሳው ዛፉ ፍሬ ለመስጠት 15 ዓመታት የሚፈጅ ቢሆንም፤ በተገኙ የምርምር ሥራዎች አማካኝት ወደ ሰባት ዓመት ማሳጠር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መፈጠሩን አንስተዋል።

ሆኖም መንግሥትና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሕብረተሰቡን በማገዝ መስራት ቢቻል፤ ከሀገር ውስጥ አልፎ ለውጭ ገበያ መቅረብ የሚችል ሃብት መሆኑን ተናግረዋል።

በተለይም ምርቱ በቀላሉ የሚገኝ እንደመሆኑ መጠን ከውጭ የሚገባውን ምርት በማስቀረት በኩል ካለው አስተዋፅኦ ባሻገር የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት ኢትዮጵያ ተጠቃሚ እንደምትሆን ገልጸዋል።

ከዚህ ባለፈም የጎንዮሽ ጉዳት የሚያስከትሉ የዘይት ምርቶችን በመተካት ትልቅ ድርሻ እንደሚኖር አመላክተዋል።

(አሐዱ ሬድዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...

የእግር ኳስ ዳኝነት በኢትዮጵያ

ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ግዮን መጽሔት :- እግር ኳስ...

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...