በአዲስ አበባ ከተማ የኃይል መቆራረጥን ለማስቀረት በተካሄደ ምርመራ ከ26 ሺሕ በላይ ችግሮች መገኘታቸው ተገለጸ

Date:

ሁለት ወራትን ባስቆጠረው በቴክኖሎጂ የታገዘ ምርመራ በአዲስ አበባ ከተማ የኤሌክትሪክ መስመሮች ላይ ከ26 ሺሕ በላይ ከባድ እና ቀላል ችግሮች እንደተገኙ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።

የኃይል መቆራረጥ ድግግሞሽን ወደ ዜሮ ለማውረድ በሚደረገው ጥረት የ100 ቀን እቅድ ተይዞ በሥራ ሂደት ላይ እንደሚገኝ ተቋሙ ለአሐዱ በላከው መረጃ አመላክቷል፡፡

በጂ.ፒ.ኤስ በታገዘ ቴክኖሎጂ በሚደረገው የምርመራ ሂደት በከተማዋ ባሉ 152 የመካከለኛ ኃይል ማስተላለፊያ መሥመሮች እና መስመሮቹን በሚሸከሙ 49 ሺሕ 581 ምሰሶዎች ላይ ቅድመ ምርመራ ተደርጎ፤ 26 ሺሕ 559 ከባድና ቀላል ችግሮች መገኘታቸውንም ገልጿል፡፡

ቅድመ ምርመራው ሲከናወን በአንድ ምሰሶ ወይም መስመር ላይ ከአንድ በላይና ተደጋጋሚ ግኝቶች እንደሚያጋጥሙ የተገለጸ ሲሆን፤ ለተደጋጋሚ የኃይል መቆራረጥ መንስኤ ከሆኑ ዋነኞቹ የግኝት ነጥቦች መካከል በ7 ሺሕ 521 ቦታዎች ላይ የዛፎች ንክኪ እና 6 ሺሕ 399 የሚሆኑት ደግሞ መቀየር የሚያስፈልጋቸው ምሰሶዎች መሆናቸው ተመላክቷል።

ከዚህ በተጨማሪም 6 ሺሕ 338 የረገቡ መስመሮች ተገኝተዋል የተባለ ሲሆን፤ 2 ሺሕ 427 መሥመሮች ደግሞ ከግንባታዎች ጋር እንዲሁም እርስ በእርሳቸው ከሚገባው ፍጥነት በላይ የተቀራረቡ ናቸው ተብሏል፡፡

እስከ አሁን 29 በመቶ ለሚሆኑት ወይም ለ7 ሺሕ 663 ችግሮች አስፈላጊው ማስተካከያ የተደረገ ሲሆን፤ ከ10 ሺሕ በላይ ትራንስፎርመሮች ላይ ደግሞ ምርመራ ተደርጎ ከ7 ሺሕ በላይ የሚሆኑት መጠነኛ ችግሮች መገኘታቸውና ማስተካከያ እየተደረገባቸው እንደሚገኝ ገልጿል።

በሌላ በኩል በከተማዋ ከፍተኛ የኃይል ጭነት ባለባቸውና በሌለባቸው የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች መካከል ከበዛው ወደ አነሰው በማስተላለፍ የኃይል ማቻቻል ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ተቋሙ አስታውቋል።

የኃይል መቆራረጥን ወደ ዜሮ ለማድረስ በተያዘው የ100 ቀን እቅድ መሠረትም በቅድሚያ አዲስ አበባ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ የተሰራ ቢሆንም፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከአዲስ አበባ ውጪ በሚገኙ ሪጅኖች 561 የቴክኒክ ባለሙያዎችን በማሰማራት አጠቃላይ ካሉት 909 የመካከለኛ መስመሮች ውስጥ እስካሁን ለ192 ያህሉ ምርመራ መጠናቀቁ ተገልጿል።

በዚህም መሠረት 193 ሺሕ የሚሆኑ መስመሮች ላይ ከባድና ቀላል ግኝቶች የተገኙ ሲሆን፤ ምርመራው ሲጠናቀቅ ከዚህም በላይ ሊሆን እንደሚችል ጠቁሟል።

(አሐዱ ሬድዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...