በጋምቤላ ክልል ያመረቱትን ወርቅ ሪፖርት እንዲያደርጉና ግዴታቸውን እንዲወጡ ተባለ

Date:

በጋምቤላ ክልል ያመረተውን ወርቅ ለክልሉ በሪፖርት የማያሳውቅና ምርት ለመጀመር ለዝግጅት ብቻ ስምንት ዓመት የፈጀበት ሁለት የወርቅ ኩባንያዎች በውላቸው መሰረት ግዴታቸውን እንዲወጡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሳሰበ።

ምክር ቤቱ ይህንን ማሳሰቢያ የሰጠው የኢንዱስትሪና ማዕድን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በሦስት መቶ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ዲማ ወረዳ ተጉዞ የሁለቱን ከፍተኛ ወርቅ አምራች ድርጅች የስራ እንቅስቃሴ ከገመገመ በኋላ ነው።

በዚህም ቋሚ ኮሚቴው ባደረገው ግምገማ በጋምቤላ ክልል አኙዋክ ዞን ድማ ወረዳ የሚገኙ ኢትኖ ማይኒንግ እና ስቴላ ለተባሉ ሁለት ከፍተኛ ወርቅ አምራች ኩባንያዎች በገቡት ውል መሰረት ግዴታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ አሳስቧል።

ኢትኖ-ማይኒንግ የተቋቋመበት ጊዜ ረጅም ቢሆንም የማምረት አቅሙ በሚፈለገው ደረጃ አለመሆኑ፣ ሠራተኞች ክፍያው ከስራው አንጻር አነስተኛ መሆኑና ፋብሪካው ያመረተውን ወርቅ ለክልሉ በሪፖርት የማያሳውቅ መሆኑን ቋሚ ኮሚቴው በእጥረት በማንሳት ኩባንያው በገባው ውል መሰረት ግዴታውን በአግባቡ እንዲወጣ ከቋሚ ኮሚቴው ማሳሰቢያ ተሰጥቶታል።

በአንጻሩ ኢትዮ-ማይኒንግ ኩባንያ ለ338 ሠራተኞች የሥራ እድል መፍጠሩ፣ ለሰራተኞች ደመወዝ ከ15ዐ እስከ 25ዐ ዶላር መክፈሉ፣ ከቴክሎጂ ሽግግር አኳያ ለሠራተኞች ስልጠና መስጠቱን ቋሚ ኮሚቴው በጥንካሬ ገምግሟል።

ኩባንያው ከማህበረሰብ አገልግሎት አኳያ ለህክምና አገልግሎት መኪና መተባበሩ፣ ንፁህ የመጠጥ ውሃ ለማቅረብና የከርሰ ምድር ውሃ ለማውጣት ቅድመ ዝግጅት ማድረጉ፣ ፋብሪካው በቀን 16 ቶን ወርቅ አዘል ድንጋይ የሚያመርት መሆኑና በወር ከ5 እስከ 7 ኪሎ ግራም ወርቅ የሚያመረት መሆኑም በጥንካሬ ተወስዶለታል።

በ2ዐዐዐ ዓ.ም ከፌደራል ፍቃድ በማግኘት በክልሉ ሥራ የጀመረው ስቴላ ከፍተኛ ወርቅ አምራች ኩባንያ በበኩሉ ከፍተኛ አምራች ሆኖ ሳለ የሚያመረተው ከልዩ አነስተኛ አምራቾች እኩል በወር 1 ኪሎ ግራም መሆኑ፣ ከ2ዐዐዐ ዓ.ም እስከ 2ዐዐ8 ዓ.ም ድረስ ማዕድን ለማውጣት በዝግጅት ብቻ 8 ዓመት የፈጀ መሆኑን ቋሚ ኮሚቴው በእጥረት በማንሳት ማስተካከያ እንዲያደርግና በውሉ መሰረት ግዴታውን በአግባቡ እንዲወጣ ቋሚ ኮሚቴው ማሳሰቢያ ሰጥቶታል።

በአንጻሩ ስቴላ ከፍተኛ ወርቅ አምራች ኩባንያ እስካሁን ድረስ ለ13 ሴት እና ለ90 ወንድ በድምሩ ለ103 ሠራተኞች የስራ ዕድል መፍጠሩ፣ ለሰራተኞች ወር ደመወዝ ከ25,000.00 ብር እስከ 60,000.00 ብር የሚከፍል መሆኑ፣ ከፌደራል ዋና መስሪያ ቤት ጋር በ2000 ዓ.ም ውል በፈረመው መሰረት ለብሔራዊ ባንክ የተመረተውን የወርቅ ምርት የሚያስገባ መሆኑ በጥንካሬ ተነስቶለታል።

ከወርቅ ኩባንያወች በተጨማሪም በጋምቤላ ክልል ዲማ ወረዳ የሚገኙ የማዕድን ፋብሪካዎች በዘርፉ ሀገሪቱ ካስቀመጠችው የዕድገት አቅጣጫ አኳያ በሚፈለገው ደረጃ እያመረቱ ባለመሆኑ ባለሀብቶቹ ከመንግሥት እና ከማህበረሰቡ ጋር ቅንጅት በመፍጠር መስራት እንዳለባቸውና የክልሉ አመራርም አስፈላጊውን ክትትል በማድረግ ከፌደራል ጋር ተቀናጅቶ እንዲሰራ የቋሚ ኮሚቴው የመስክ ምልከታ ቡድን መሪ አቶ ፍቃዱ ሞሲሳ ማሳሰባቸውን አዲስ ማለዳ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መረጃውን ተመልክታለች።

አዲስ ማለዳ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...