በፀሐይ ኃይል የሚሰራው ግዙፉ የመኪና ማጓጓዣ መርከብ የመጀመሪያ ጉዞውን አጠናቀቀ

Date:

የዓለማችን ትልቁ በፀሐይ ኃይል የሚሰራ የመኪና ማጓጓዣ መርከብ “ዩዋን ሃይ ኮው” (Yuan Hai Kou) የመጀመሪያ ጉዞውን በተሳካ ሁኔታ አጠናቆ በግሪክ ፒሬየስ ወደብ መድረሱን የቻይና ኮስኮ ሺፒንግ ኮርፖሬሽን ሊሚትድ (China COSCO Shipping Corporation Limited) አስታወቀ። መርከቡ 4,000 የቻይና ተሽከርካሪዎችን ጭኖ በሰላም ደርሷል ነው የተባለው፡፡

ይህ ዘመናዊ መርከብ በፀሐይ ኃይል የሚሰራ በመሆኑ ለአካባቢ ጥበቃ ትልቅ አስተዋፅኦ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። የ”ዩዋን ሃይ ኮው” መምጣት በባህር ትራንስፖርት ኢንዱስትሪ ውስጥ የዘላቂነት እና የቴክኖሎጂ እድገት ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል ነው የተባለው።

የቻይና ኮስኮ ሺፒንግ ኮርፖሬሽን ሊሚትድ ይህ መርከብ የካርበን ልቀትን በመቀነስ እና የአካባቢን ተፅእኖ በመቀነስ ረገድ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ገልጿል።

የመርከቡ የመጀመሪያ ጉዞ ስኬታማ መሆን የቻይናን በባህር ትራንስፖርት ዘርፍ ያለውን የቴክኖሎጂ አቅም የሚያሳይ ሲሆን፣ ለወደፊት ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑ የትራንስፖርት አማራጮችን ለማስፋፋትም መንገድ ይከፍታል ተብሎለታል።

menahriafm

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...

የኢትዮጵያ አጠቃላይ ብድር 51.8 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ይፋ ሆኗል

ኢትዮጵያ  በድጋፍ መልክ ከአሜሪካ በየዓመቱ  በመንግስት በኩል ፈሰስ የሚደረግ...