በ120 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነቡ ናቸው

Date:

ለ22 ዓመታት ለኢትዮጵያ የፊልም ኢንዱስትሪ  ትልቅ አስተዋፅዖ እንዳበረከተ የሚነገርለት ዓለም ሲኒማ፤ አሁን ደግሞ ለመገናኛና አካባቢው የፊልም ተመልካች በማራቶን የገበያ ማዕከል ሁለተኛ ፎቅ ላይ ደረጃውን የጠበቁ  ሁለት ሲኒማ ቤቶችን  ከፍቷል፡፡

ቅዳሜ   በተደረገው የምርቃት ስነስርዓት ላይ የአዲስ አበባ ባህልና ኪነጥበብ ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ሂሩት ካሣ እንዲሁም የኪነጥበብ ባለሙያዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

ዓለም ሲኒማ በመገናኛ ሁለት ደረጃቸውን የጠበቁ ሲኒማ ቤቶችን በ120 ሚሊየን ብር ወጪ የገነባ ሲሆን፤ በአጠቃላይ ከ550 በላይ ተመልካቾችን የማስተናገድ አቅም እንደለው ተነግሯል፡፡

ሲኒማ ቤቶቹ  ከፍተኛ የምስል ጥራት ያላቸው፣ ዘመናዊ ሳውንድ ሲስተም የተገጠመላቸው እንዲሁም ምቹና ውብ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡

በሁለቱም ሲኒማ ቤቶች ከሐምሌ 26 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ  የተለያዩ ሀገርኛ ፊልሞች ለዕይታ ይቀርባሉ ተብሏል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

“ሕገ መንግሥታዊ ተቃርኖዎች”:-  ከዳኛ ፍሬሕይወት ሳሙኤል ጋራ ውይይት

ዳኛ ፍሬሕይወት ሳሙኤል በተለይ በ1997 ዓ.ም በተደረገው ምርጫ 97...

የ12ኛ ክፍል የፈተና ቀን ታወቀ

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሠርተፊኬት (12ኛ ክፍል ፈተና) ከሰኔ...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሳልቫ ኬር ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አደረጉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት...

አሜሪካ ኤርትራ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ልታነሳ ነው !

የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር፣ አሜሪካ ከኤርትራ ጋር ያላትን ግንኙነት...