በንብ ኢንሹራንስ ኩባንያ በቀድሞው ምርጫ ላይ ግድፈቶች በመገኘታቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ውድቅ አድርጎት እንደነበር ይታወሳል። የጥቅምት 23 ቀን 2017 ዓ.ም. ምርጫ ከተሻረ በኋላ እንደገና በተጠራው ጠቅላላ ጉባዔ ዘጠኝ አዳዲስ የቦርድ አባላት ተመርጠዋል።
ብሔራዊ ባንክም አዲሶቹን የቦርድ አባላት ሹመት ባለፈው ሳምንት ያፀደቀ ሲሆን፣ በዚህም መሰረት አዲስ የቦርድ ሊቀመንበር እንደሚሰየም ተገልጿል። ከአዲሶቹ አባላት መካከል አንዱ ብቻ ከቀድሞው ቦርድ የተካተተ ሲሆን፣ ሌሎቹ በሙሉ አዲስ ሲል የዘገበው ሪፖርተር ነዉ።
