#በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ በሚገኘው ኢንዱስትሪ ፓርክ የተሰማሩና ጦርነትን ሸሽተው ከሀገር የወጡ ባለሀብቶች ማሽኖቻቸውን ከሀገር ለማስወጣት ጥያቄ ማቅረባቸውን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ።
የኮርፖሬሽኑ የኦፕሬሽንና ማኔጅመንት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ካሚል ኢብራሂም እንደተናገሩት በጦርነት ወቅት ከአገር ሸሽተው የሄዱ ባለሀብቶችን ለረዥም ጊዜያት በኢንተርኔትና በአካል በመገናኘት ኩባንያዎቻቸው ተመልሰው ወደ ልማት እንዲገቡ ጥረቶች ቢደረጉም ፍላጎት አለማሳየታቸውን ገልጸዋል፡፡
“በአጠቃላይ አገራዊ ምርት የተመዘገቡ ማሽኖችን ወደ ሌላ አገር ከሚወስዱ፣ በአገር ውስጥ ወደ ሌላ አካባቢ በማዘዋወር ለማሠራት ጥያቄ አቅርበን እየጠበቅን ነው” ሲሉ የኮርፖሬሽኑ የኦፕሬሽንና ማኔጅመንት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ካሚል ኢብራሂም ተናግረዋል።
ወ/ሮ ሶስና ጌታሁን የተባሉ የቋሚ ኮሚቴው አባል በበኩላቸው፣ መቀሌ የነበሩ ኢንቨስተሮች እዚያው መቆየት ካልፈለጉ ወደ ሌሎች አከባቢዎች ለማዘዋወር የቀረበውን ጥያቄ ተችተዋል፤ “ኢንቨስተሮቹ ቦሌ ለሚ ወይም አዳማ እንዲያለሙ ለማድረግ እየተሠራ ነው የሚለው ምላሽ ተገቢ አይደለም” ማለታቸው ተጠቁሟል።
