ቫይደም ሄልዝ በአዲስ አበባ ቢሮ ከፈተ

Date:

በህንድ ሀገር መሰረቱን ያደረገው ቫይደም ሄልዝ በአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ቢሮውን ከፈተ

በውጭ ሀገራት ህክምና ለሚያስፈልጋቸው ህሙማን በማማከርና የጉዞ ሁኔታዎችን በማመቻቸት የሚታወቀውና በህንድ  ሀገር መሰረቱን ያደረገው ቫይደም ሄልዝ በአዲስ አበባ ቅርንጫፉን በይፋ እንደከፈተ አስታውቋል።

“ቫይደም ሄልዝ አለም አቀፍ ልምዱን ይዞ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ ከህክምና ጉዞ ጋር ተያይዘው የሚታዩ ክፍተቶችን ለመሙላትና ለታካሚዎችና ለቤተሰቦቻቸው እፎይታን ለመስጠት ያለመ” መሆኑን የቫይደም ሄልዝ መስራች እና ስራ አስኪያጅ ሚስተር ፓንኬጅ ቻንድራ ተናግረዋል።

ቫይደም ሄልዝ በህንድ፣ ቱርክ፣ ታይላንድ፣ ዱባይ፣ ጀርመን፣ ቱኒዚያ፣ ግብፅ፣ ሲንጋፖር፣ ማሌዥያ እና ደቡብ ኮሪያ ከሚገኙ ከ 8,000 በላይ ዶክተሮች ጋር ግንኙነት ያለው ሲሆን እስካሁን ድረስም በዓለም ዙሪያ ከ 100,000 በላይ ታካሚዎች ህክምና እንዲያገኙ አስተዋጽኦ እንዳደረገም ተገልጿል።

ለተጨማሪው:https://t.me/E

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...