ትራምፕ በኢራን የኒውክሌር ድርድር ላይ በተዘዋዋሪ እንደሚሳተፉ ገለጹ

Date:

ዶናልድ ትራምፕ በጄኔቫ በሚጀመረው በኢራን እና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል በሚካሄደው ድርድር ላይ በተዘዋዋሪ እንደሚሳተፉ ተናግረዋል።

በስዊዘርላንድ የሚካሄደው ይህ ሁለተኛው ዙር ድርድር የተጀመረው፤ ኢራን ፀረ-መንግሥት ተቃውሞዎች ላይ በወሰደችው የኃይል እርምጃ እና በኒውክሌር መርሃ ግብሯ ላይ በቀጠለው ውዝግብ ምክንያት ተደጋጋሚ ወታደራዊ ዛቻዎች ሲሰነዘሩባት ከቆዩ በኋላ ነው።

በኦማን አሸማጋይነት የሚካሄደው የዛሬዉ ስብሰባ፤ በኒውክሌር መርሃ ግብሩ እና በዩናይትድ ስቴትስ የተጣሉ የምጣኔ ሀብት ማዕቀቦች ሊነሱ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ኢራን ገልጻለች።

ዋሽንግተን በበኩሏ ቀደም ሲል እንደ ሚሳዔል ክምችት ያሉ ሌሎች ጉዳዮችንም መወያየት እንደምትፈልግ አመልክታለች።

ድርድሩ‹‹በጣም አስፈላጊ›› መሆኑን የጠቀሱት ትራምፕ፤ ቴህራን በዚህ ወቅት ለመደራደር ፍላጎት ያሳየችው በተለያዩ ምክንያቶች ተገፋፍታ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ትራምፕ፤ስምምነት ላይ አለመድረስ የሚያስከትለውን መዘዝ ይፈልጋሉ ብዬ አላስብም ያሉ ሲሆን፤ባለፈው ክረምት ዩናይትድ ስቴትስ የኢራን የኒውክሌር ጣቢያዎችን በደበደበችበት ወቅት፤ ኢራን በድርድር ወቅት ጥብቅ አቋም መያዝ የሚያስከትለውን መዘዝ ተምራለች ሲሉ አክለዋል።

የፕሬዝዳንቱ ዛቻዎች የመጡት ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ዩናይትድ ስቴትስ በመካከለኛው ምስራቅ ወታደራዊ ኃይል እየገነባች ባለበት ወቅት ነው።

ቢቢሲ ቬሪፋይ የሳተላይት ምስሎችን በመጠቀም የዩኤስ አብርሃም ሊንከን የአውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ በኢራን አቅራቢያ መገኘቱን አረጋግጧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...