ቻይና ለአንድ አመት ያክል የሚቆይ ከፍተኛ የጦር ሰራዊት የህክምና ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መላኳን አስታወቀች

Date:

በኢትዮጵያ ለአንድ አመት ቆይታ ግዜ የሚኖረው የህክምና እገዛ የሚያደርገ ወታደራዊ የህክምና ልዑክ ቡድን መላኩን የቻይና ብሔራዊ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።

“11ኛ ዙር የቻይና ህዝቦች ነፃነት ጦር የህክምና ረድኤት ቡድን የኢትዮጵያን መከላከያን የህክምና አገልግሎት ለመደገፍ ጉዞ ጀምሯል” ሲል ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ ጠቁሟል።

ሚኒስቴሩ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ “ይህ ወደ ኢትዮጵያ የላክነው ትልቁ ወታደራዊ የህክምና ባለሙያ ቡድን ነው” ብሏል”ቡድኑ 14 ወታደራዊ ዶክተሮችን ያቀፈ” መሆኑን አስታውቋል።

እንደ ሚኒስቴሩ መግለጫ ከሆነ ልዑክ ቡድኑ “ክሊኒካል ህክምና የህክምና ቴክኖሎጂ በሆስፒታል አስተዳደር እና የሎጀስቲክስ ድጋፍን” ጨምሮ የተለያዩ የህክምና ዘርፎች የተካተቱበት ነው “ሁሉም የልዑኩ አባላት በክሊኒካዊ ሕክምና እና በጤና እንክብካቤ አስተዳደር” ከፍተኛ ልምድ ያላቸው መሆናቸውን ጠቁሟል።

ቡድኑ ወደ ኢትዮጵያ ጉዞ ከማድረጉ በፊት አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ስልጠና ወስዷል ያለው የሚኒስቴሩ መግለጫ “እንደ ስሜትን መቆጣጠር አስቸጋሪ ህመሞችን ማከም እና ተላላፊ በሽታዎችን በመከላከል እና በመቆጣጠር ላይ ያነጣጠረ ስልጠና” ማግኘታቸውንም አመላክቷል።

ስልጠናዎቹ “በተለያዩ ሀገራት የህክምና ዕርዳታ ተልእኮዎችን የመፈጸም ችሎታቸውን በእጅጉ የሚያጠናክር ነው ሲል ገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ደቡብ ሱዳን የነዳጅ ቅድመ-ክፍያ ውሎችን እንዳትፈጽም አገደ

የለንደን ፍርድ ቤት ደቡብ ሱዳን ከአሁን በኋላ አዳዲስ የነዳጅ...

” ከ140 በላይ ጠጠር አምራች ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ ቆመዋል ” – ማህበሩ

" ካላቸው ቅሬታ ማቅረብ ይችላሉ። ግን መሬቱ መቼ እንደተወሰደባቸው...

ትራምፕ “በኢራን ላይ ሊፈጸም ታቅዶ የነበረውን ጥቃት አንፈጽምም” አሉ

ትራምፕ በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ ቁልፍ የአሜሪካ አጋር ሀገራት መሪዎች...

በነዳጅ ጭማሪ በኬንያ በተቀሰቀሰ ተቃውሞ የአራት ሰዎች ሕይወት አለፈ

በኬንያ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪን ተከትሎ በዋና ከተማዋ ናይሮቢ በጸጥታ...