አቅመ ደካማ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ነጻ የቀዶ ጥገና ህክምና አገልግሎት ከአፔክስ ኢንዲያን ሆስፒታል ጋር በመተባበር ለመስጠት መዘጋጀቱን ቢላሉል ሀበሺ የልማትና መረዳጃ እድር አስታወቀ፡፡
25ኛ የምስረታ ዓመቱን በተለያዩ መርሃ ግብሮች እያከበረ የሚገኘው ቢላሉል ሀበሺ የልማትና መረዳጃ እድር ከፍለው መታከም ለማይችሉ ዜጎች የነጻ ህክምና አገልግሎት ከሆስፒታሉ ጋር በመተባበር ማዘጋጀቱን ነው ለጣቢያችን በላከው መረጃ የገለጸው፡፡
የነጻ ህክምና አገልግሎት ከሚሰጥባቸው የህክምና አይነቶች መካከል የትልቁ አንጀትና ፊንጢጣ ካንሰር፣ የሆድ ካንሰር፣ የጉበት ካንሰር፣ የሐሞት ፊኛ ካንሰር፣ የኩላሊት ካንሰር፣ የወንድ የዘር ፍሬ ካንሰር፣ የፕሮስቴት ካንሰር እንዲሁም የጡት ካንሰርን ጨምሮ ሌሎችም የካንሰር ህመሞች የነጻ ቀዶ ጥገና ህክምና ማዘጋጀቱን አስረድቷል፡፡
በተጨማሪም ከካንሰር ውጪ የሆኑ ህመሞች ማለትም የሐሞት ፊኛ በሽታዎች፣ የዘር አካል እብጠት፣ የደም ሥር እብጠት፣ ኪንታሮት፣ የፊንጢጣ ፊስቱላ እና መሰንጠቅ፣ የሆድ እብጠቶች፣ የታይሮይድ በሽታዎች፣ የኩላሊትና የሽንት ፊኛ በሽታዎች፣ የዘር አካል እብጠት በሽታዎችን ጨምሮ ሌሎችም የነጻ ህክምና አገልግሎት የትኛውም ከፍሎ መታከም የማይችል ዜጋ ማግኘት እንደሚችል ነው ያስታወቀው፡፡
የነጻ ቀዶ ጥገና ህክምና አገልግሎቱን ለማግኘት ቢላሉል ሀበሺ የልማትና መረዳጃ እድር በማስገባት ከዛሬ ጀምሮ መመዝብ እንደሚቻል አመላክቷል፡፡
ተጨማሪ መረጃ ወደ:– 0972787878 0972797979 0987151515
በመደወል ማግኘት እንደሚቻል ተቋሙ ገልጿል።
