የሀገሪቱ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ኔቱምቦ ናንዲ ከ2026 በሃገሪቱ ባሉ በሁሉም የመንግስት ከፍተኛ ተቋማት ዩኒቨርስቲና ኮሌጅ ትምህር በነፃ እንዲሰጥ ተወሰነ ።
ፕሬዘዳንቷ ሀሙስ ማምሻውን ባደረጉት ንግግር ሀገሪቱ የሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እና የቴክኒክ ኮሌጆች “ምንም የምዝገባ [ወይም] የትምህርት ክፍያ አይከፍሉም ለተማሪዎቹም የምግብና መሰረታዊ ወጭዎች በመንግሥት ይሸፈናል ።አቅም ለሌላቸዉም ድጎማ እና የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል ።
አክለዉም የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት በሁሉም የሀገሪቱ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ነፃ በሚሰጥባት ናሚቢያ ለትምህርቱ ዘርፍ ትኩረት በመስጠት ከቀጣይ አመት ጀምሮ የሀገሪቱ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በነፃ ለማስተማር መንግስታቸው ከፍተኛ በጀት መመደቡን ገልፀዋል ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነዉ ።
የ72 ዓመቷ ናንዲ-ንዳይትዋህ ከተመረጡ በኋላ በአንፃራዊነት ጠንካራ የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገበች ያለች ሲሆን በዋነኛነት በነዳጅ፣ በጋዝ እና በአረንጓዴ ሃይድሮጅን ዘርሮች ትክረት አድርገው በመስራት
ከፍተኛ የስራ አጥነት መጠንን በመቅረፍ በግብርናው ዘርፍ ኢንቨስትመንቶችን ለማሳደግ እና በሀብት ላይ ያተኮረ ኢኮኖሚ በመገንባት ለዉጥ ማምጣታቸውን ይነገራል።
