ስምረት ፓርቲ ዋና ፅህፈት ቤቱን ከፈተ

Date:

በእነ አቶ ጌታቸው ረዳ የተቋቋመው ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) የፓለቲካ ፓርቲ ዋና ፅህፈት ቤቱ በመቐለ ከፈተ።

በተጨማሪም ፓርቲድ የመቐለ እና ደቡባዊ ምስራቕ ዞን ቅርንጫፍ ቢሮዎች ከፍቷል።

ፓርቲው እንዳስታወቀው ዋና ፅህፈት ቤቱ በመቐለ በመክፈት የፓለቲካ ስራውን በግልፅ ጀምሯራ።

ፓርቲው በሁሉም የትግራይ የዞን ፣ የወረዳና ከተሞች ፓለቲካዊ ፅህፈት ቤቶች መክፈት እንደሚቀጥል አስታውቋል።

ከአንድ ወር በፊት ከኢትዮጵያ ብሄራዊ  የምርጫ ቦርድ ቅድመ እውቅና ያገኘው ስምረት ፓርቲ ለምስረታ ብቁ የሚያደርጉት አባላት መልምሎ ጨርሷል።

የክልል ፓርቲ ለመመስረት የሚስፈልገው 4 ሺህ በላይ መስራች አባላት መልምሎ ለይፋዊ ምስረታ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ተነግሯል ።

ስምረት ፓርቲ በቀጣዩ የነሀሴ ወር 2017 ዓ.ም በትግራይ ይፋዊ ምስረታ በማከናወን ከቅድመ እውቅና ወደ ሙሉ እውቅና እንደሚሸጋገር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...