አዋሽ ኢንሹራንስ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በመተባበር መንገደኞች በጉዟቸው ወቅት ለሚያጋጥሟቸው ያልተጠበቁ የጤና እክሎች ዋስትና የሚሰጥ ዘመናዊ የጉዞ ጤና ኢንሹራንስ አገልግሎት በይፋ ማስጀመሩን አስታወቀ።
መንገደኞች የአየር መንገዱን የሞባይል መተግበሪያ (Mobile App) በመጠቀም ብቻ አገልግሎቱን በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ ተብሏል።
በጉዞ ወቅት ለሚከሰቱ ድንገተኛ የጤና እክሎች እና ሌሎች ተያያዥ ችግሮች አስተማማኝ የኢንሹራንስ ሽፋን ይሰጣል።
የሁለቱን ግዙፍ ተቋማት ስትራቴጂካዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እና የደንበኞችን ምቾት ለማረጋገጥ ያለመ እንደሆነ ተነግሯል።
አዋሽ ኢንሹራንስ እስከ ታህሳስ 2025 (እ.ኤ.አ) ድረስ አጠቃላይ ሀብቱ ከ13 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን ገልጿል።
