የሚኒሶታ ግዛቷ ተወካይ ኢልሃን ዑመር በከተማው አዳራሽ ንግግር እያደረጉ ሳለ ጥቃት ደርሶባቸዋል።
ጥቃት ለማድረስ የሞከረው ግለሰብ ወዲያውኑ ተይዟል ቢባልም ለአሜሪካ ባለስልጣናት ደህንነት ስጋት የደቀነ ክስተት ሆኗል።
ኢልሃን ዑመርም ምንም ዓይነት ጉዳት ያልደረሰባቸው ሲሆን ህዝባዊ ተቃውሞው በበረታበት ሰዓት የተፈፀመ ድርጊት መሆኑ ግን ስጋቱን በሚኒሶታ ከፍ አድርጎታል።
ምንነቱ ያልታወቀ ቁስ ዑመረ ላይ ተጠርጣሪው ረጭቶባቸዋል።
ዜናው እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረሰ ግለሰቡ ላይ ክስ ስለመመሰረቱ የአካባቢው ባለስልጣናት ያሉት ነገር የለም።
ከአደጋው በፊት ኢልሃን ዑመር የአሜሪካ የሰደት እና ጉምርክ ተቆጣጣሪዎች ከሚኒያፖሊስ መወጣት እንዳለበቸው ንግግር ሲያደርጉ ነበር።
የአይሰ ሀይሎች ሀዝቡ ላይ በሚያደርሱት ጫና ምክንያት ተቃውሞ ገጥሟቸዋል።
ዋይት ሀውስ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ በጉዳዩ ላይ ያለው ነገር የለም።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው።
