አሜሪካ ለሦስተኛ ቀን በኢራን ላይ ጥቃት መፈጸሟን ተከትሎ የኢራን ጦር ኃይል ማዕከላዊ ዕዝ የሆርሙዝ ወሽመጥ ነዳጅጫኝ እና የንግድ መርከቦች ጨምሮ ለሁሉም የባሕር ላይ እንቅስቃሴ ዝግ መሆኑን አስታወቀ።ባ
ለፉት ቀናት አሜሪካ እና ኢራን ጥቃት ሲፈጽሙ የቆዩ ሲሆን፣ አሜሪካ በኢራን ውስጥ የሚገኙ ዒላማዎችን ስትመታ ኢራንበአጸፋው በፋርስ ባሕረ ሰላጤ አገራት ውስጥ በሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች እና በእስራኤል ላይ ጥቃት ፈጽማለች።ረቡ
ዕ ሌሊት በአሜሪካ የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን ከዘጋች በኋላ አብዮታዊ ዘቡ በሕገወጥ መንገድለማለፍ ሞክረዋል ያላቸውን ሁለት መርከቦችን መምታቱን አስታውቋል።የኢራ
ን ወታደራዊ ማዘዣ የሆነው ኻታም አል-አምቢያ እንዳስታወቀው “በቀጣናው ባለው አለመረጋጋት ምክንያት የሆርሙዝ ወሽመጥለሁሉም መርከቦች ተዘግቷል” በማለት ለማለፍ የሚሞከሩ መርከቦች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ አስታውቋል።የወሳኙ
የባሕር መተላለፊያ መዘጋት ለወራት ጋብ ብሎ የነበረው የአሜሪካ እና ኢራን ጦርነት እየተባባሰ መሆኑን የሚያመለክትነው። ከፍተኛ መጠን ያለው የዓለም የነዳጅ ፍጆታ የሚተላለፍበት ወሽመጥ በመዘጋቱ የነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተከስቷል።ጦርነቱ
በየካቲት ወር መጨረሻ ገደማ ከተቀሰቀሰ በኋላ ኢራን ሆርሙዝን ሙሉ ለሙሉ ከመዝጋት ይልቅ በመርከቦች እንቅስቃሴላይ ገደቦች ጥላ ቁጥጥር ስታደርግ ነበር። በተጨማሪም የባሕር መተላለፊያውን የሚመለከት አዲስ ሕግ እና አሠራር በማውጣት ሆርሙዝንበቁጥጥሯ ስር ለማስገባት ስትሠራ ቆይታለች።ይህ የኢራን
ውሳኔ የተሰማው ኢራን የአሜሪካ የጦር ሄሊኮፕተርን መትታ ከጣለች በኋላ ከአሜሪካ ተደጋጋሚ ጥቃት ስለተፈጸመባትነው። ሆርሙዝ ወሽ
መጥ ዓለም ለፍጆታው ከሚያስፈልገው 20 በመቶው ነዳጅ ዘይት እና ጋዝ ከባሕረ ሰላጤው አገራት በመነሳት በየቀኑየሚተላለፍበት ወሳኝ የባሕር መስመር ነው።
