የኢራን እና የአሜሪካ ግጭት ከዕለት ወደ ዕለትእየተባባሰ ባለበት በአሁኑ ወቅት ፕሬዝዳንት ትራምፕ ዛሬም በድጋሚ በኢራን ላይ ከባድ ጥቃት እንደሚፈጸም እና በቅርቡም አሜሪካየኻርግ ደሴትን እንደምትቆጣጠር አስታወቁ።ፕሬ
ዝዳንቱ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩ“ባሕር ኃይሏ፣ የአየር ኃይሏ፣ የአየር መከላከያ ሥርዓቷ እና ሁሉም የጥቃት አቅሟ” ወድሟል ያሏት ኢራንን ዳግም ዛሬ “ሌሊትበኃይለኛው ትመታለች” ብለዋል። “ቬን
ዙዌላ ላይ እንዳደረግነው ብዙም ሳይቆይየኻርግ ደሴትን እና ሌሎች የነዳጅ መሠረተ ልማቶችን እንይዛለን፤ በዚህም የኢራንን የነዳጅ እና የጋዝ ገበያን ሙሉ ለሙሉ እንቆጣጠራለን”ሲሉ ዕቅዳቸውን አሳውቀዋል። ከኢራ
ን ጋር የሚደረገው ጦርነት ከተጀመረበት ጊዜአንስቶ ፕሬዝዳንት ትራምፕ የኢራን ዋነኛው የነዳጅ ማስተላለፊያ የሆነውን ኻርግ ደሴትን እንደሚቆጣጠሩ በተደጋጋሚ ሲናገሩ ነበር።በሰሜና
ዊ የባሕረ ሰላጤው አካባቢ የሚገኘው ኻርግደሴት ኢራን ወደ 90 በመቶ የሚሆነውን የነዳጅ ምርቷን ለቀሪው ዓለም የምታቀርብበትት ዋና መተላለፊያ ነው።ደሴቱ ከ
ኢራን የባሕር ዳርቻ አቅራቢያ የሚገኝሲሆን፣ ወደ ሁለት ሚሊዮን በርሜል መጫን የሚችሉ ግዙፍ ድፍድፍ ነዳጅ ጫኝ መርከቦች ላይ ነዳጅ ለመሙላት የሚያስችል ጥልቅየውሃ ክፍል አለው።
