ኢትዮጵያና ሩዋንዳ የመከላከያ ትብብራቸውን ለማዘመን ተስማሙ

Date:

ኢትዮጵያ እና ሩዋንዳ ያላቸውን ታሪካዊ የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ በማጠናከር፣ የመከላከያ ዘርፉን በዘመናዊ የሰው ሠራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) ቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ መግባባት ላይ ደርሰዋል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ ከሩዋንዳ መከላከያ ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጄኔራል ሮናልድ ሪቪዋንጋ ጋር በነበራቸው ውይይት፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የቆየ ወታደራዊ ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር መክረዋል።

በውይይቱ ወቅት ሁለቱም ወገኖች ወቅታዊ የደህንነት ተግዳሮቶችን ለመቋቋም ወታደራዊ ተግባራትን በቴክኖሎጂ ማዘመን ወሳኝ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። በተለይም ወታደራዊ ስምሪቶችን በፈጣንና በዘመናዊ መንገድ መምራት፤ የደህንነት ስጋቶችን ቀድሞ ለመተንበይና ለመተንተን የሰው ሠራሽ አስተውሎትን መጠቀም፤ የላቁ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የሀገራቱን የመከላከል አቅም ማጎልበት በሚሉ ነጥቦች ላይ የጋራ መግባባት ተፈጥሯል።

ይህ አዲስ የትብብር አቅጣጫ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ወታደራዊ ዲፕሎማሲ ከማጠናከሩ ባለፈ፣ ለአፍሪካ ቀንድና ለምስራቅ አፍሪካ ቀጠናዊ ሰላምና ደህንነት ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው ታምኖበታል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...