“ኢትዮጵያ የባሕር በር አያስፈልጋትም የሚል የፖለቲካ ፓርቲ ካለ መሰረዝ ነው ያለበት”

Date:


ኢትዮጵያ የባሕር በር አያስፈልጋትም የሚል የፖለቲካ ፓርቲ ካለ ከፓርቲነት ተሰርዞ ከፖለቲካው ምዕራፍ መውጣት እንዳለበት የኢዜማ አመራርና የአዲስ አበባ ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ ግርማ ሰይፉ ተናገሩ።

አቶ ግርማ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ የሀገሪቱን የባሕር በር የማረጋገጥ ጉዳይ በቀጣይ ሕገ-መንግሥቱ በሚሻሻልበት ወቅት ትኩረት ተሰጥቶት የመንግሥት ግዴታ ተደርጎ ሊደነገግ ይገባል።

ለዚህም እንደ ምሳሌ ያነሱት የግብፅ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 19 የናይልን ውኃ ደኅንነት ማስጠበቅ የመንግሥት ግዴታ መሆኑን እንደሚደነግግ ጠቅሰው፣ በኢትዮጵያም የባሕር በርን ማስጠበቅ ሕገ-መንግሥታዊ ግዴታ ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።


ብሔራዊ ጥቅምን የማስከበር ኃላፊነት በመንግሥት ላይ መጣል እንዳለበት የገለጹት አቶ ግርማ፤ ከዚህ ብሔራዊ ጥቅም በተቃራኒ የሚቆሙ አካላትን መቆጣጠር የመንግሥት ግዴታ ሊሆን እንደሚገባም አመልክተዋል።

የባሕር በር ጥያቄ ከፖለቲካ ወገንተኝነት ባለፈ የሀገር ህልውና ጉዳይ መሆኑንና ማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት ለዚህ ግብ መሳካት ቅድሚያ መስጠት እንዳለበትም በአጽንኦት ገልጸዋል።

ጋዜጣ_ፕላስ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...