በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በተከሰተው አዲስ የኤቦላ ወረርሽኝ ምክንያት፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ አሥር የአፍሪካ ሀገራት ለበሽታው ተጋላጭ መሆናቸውን የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከል አስታውቋል።
እነዚህም ሀገራት
🇷🇼 ሩዋንዳ፣
🇰🇪 ኬንያ፣
🇹🇿 ታንዛኒያ፣
🇦🇴 አንጎላ፣
🇧🇮 ቡሩንዲ፣
🇨🇫 መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ፣
🇨🇩 ኮንጎ ሪፐብሊክ፣
🇪🇹 ኢትዮጵያ፣
🇸🇸 ደቡብ ሱዳን እና
🇿🇲 ዛምቢያ ናቸው።
ከኢትዮጵያ በስተቀር የተቀሩት ዘጠኙ ሀገራት የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ወይም የኡጋንዳ ድንበር ተጋሪ በመሆናቸው ስጋቱ የበለጠ ከፍ ያደርገዋል ተብሏል።
የአፍሪካ CDC እና የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ወረርሽኙን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከ314 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ እየጠየቁ ሲሆን፤ ከዚህ ውስጥ 54 ሚሊዮን ዶላሩ ለተጠቀሱት 10 ከፍተኛ ተጋላጭ ሀገራት ይመደባል ተብሎ ይጠበቃል።
የዓለም ጤና ድርጅት በቀጠናው ያለውን የኤቦላ ስጋት ደረጃ ወደ “እጅግ ከፍተኛ” ሲል ከፍ አድርጎታል።
Source : Anado
