ኢትዮጵያ የእቴጌ ጥሩወርቅ ዉቤ ወለባ (የፀጉር ጌጥ) በክብር ተረከበች

Date:

ኢትዮጵያ በዝርፊያ ከሀገር ዉጭ ተወስዶ የነበረው የእቴጌ ጥሩወርቅ ዉቤ (የአጼ ቴዎድሮስ ባለቤት የፀጉር ጌጥ በክብር ተረከበች፡፡

በርክክቡ መርሃ ግብር ንግግር ያደረጉት አበባው አያሌው (ረ/ፕ) የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬከተር፣ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ በተለያዩ ምክንያቶች ከሀገር ውጭ የተወሰዱ በርካታ ቅርሶችን ማስመለስ ተችሏል፤ ቀሪዎችንም ለማስመለስ በከፍተኛ ትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ንብረት የሆኑ ነገር ግን የተዘረፉ ቅርሶቻችንን ለማስመለስ በድርድርም ሆነ በክርክር እስካሁን 72 ቅርሶችን ለማስመለስ ተችሏል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

የተዘረፉ ቅርሶችን ለማስመለስ ይረዳ ዘንድ ባለስልጣን መ/ቤቱቀደም ሲል በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ተዋቅሮ ሳለ ብሔራዊ የቅርስ አስመላሽ ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ስራ መገባቱን ተከትሎ ሀገርን የሚያኮራ ስራ ሰርተዋል፣ እየሰራም ይገኛል ብለዋል፡፡

ይህ ቅርስ ለኢትዮጵያውያን ትልቅ ትርጉም አለው ያሉት አበባው አያሌው ከብዙ ልፋትና ውጣውረድ በባለስጣኑና በኢትዮጵያን ወዳጆች፣ዜጎችና ደርጅቶች ያለሰለሰ ጥረትና ጥምረት ልመለስ ችለዋል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ንጉሳዊ በጎ አድራጎት ባለ አደራ ድርጅት ይህንን ቅርስና ከዚህን በፊትም የአጼ ተዎድሮስ ጋሻ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ለዚህም ለድርጅቱ፣ ለልዑል ኤርሚያስ ሳህሌስላሴና ባልደረቦቻቸው እንዲሁም ለዶ/ር አሉላ ፓንክርስ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በቀጣይም በተለያዩ ምክንያቶች ከሀገር ውጭ የወጡ ቅርሶቻችንን ለማስመለስ ባለስልጣን መ/ቤቱ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ከሚመለታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የተለያዩ ስልቶችን በመንደፍ በትኩረት ይሰራል ሲሉ ዋና ዳይሬክቱ ገልፀዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች፣የኢትዮጵያ አርበኞች ማህበር አባላት፣ የኢትዮጰያ ቅርስ ባለአደራ አባላት፣ የጥንታዊት ኢትዮጰያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዝዳንትና ሌሎች በላድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን ቅርሱን በማስመለስ ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ሚና ለተጫወቱት ግለሰብና ድርጅት የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡
(የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...