የዓለም አቀፉ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል (ፊፋ) ፕሬዚዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ በሩሲያ ላይ የተጣለውን ዕገዳ ሊያነሱ እንደሚችሉ አስታውቀዋል።
ሩሲያ ከዩክሬን ጋር የገባችውን ጦርነት ተከትሎ ዩክሬንን “ወራለች” በሚል ብሔራዊ ቡድኗም ሆነ የእግር ኳስ ክለቦቿ ከማንኛውም ውድድር ከሦስት ዓመት በፊት መታገዳቸው ይታወሳል።
ኢንፋንቲኖም ይህ ዕገዳ “ያመጣው ለውጥ የለም” በሚል ለማንሳት ማሰባቸውን ይፋ አድርገዋል።
ዕገዳው “ጥላቻ ብቻ” ነው ያመጣው ያሉት ኢንፋንቲኖ እርምጃው ነገሮችን ሊያሻሽላቸው ይችላል የሚል ሃሳብ አላቸው።
የኢንፋንቲኖን አስተያየት ተከትሎ የዩክሬን ስፖርት ሚኒስትር ማትቪ ቢድኒ፥ ኢንፋንቲኖን “ሃላፊነት የጎደላቸው” በማለት ወርፈዋቸዋል።
ሚኒስትሩ “እግር ኳሱን ህፃናት ከሚገደሉበት እውነታ ጋር ሊለያዩት ሞክረዋል” ሲሉ የፕሬዚዳንቱን ሃሳብ ተችተዋል።
