ኤርትሪያ ከኢጋድ አባልነቷ ሙሉ በሙሉ መውጣቷን አስታውቃለች

Date:

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት ኢጋድ የኤርትራ መንግስት ከድርጅቱ ለመውጣት ያሳለፈውን ውሳኔ በጸጸት ገልጿል።

የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ታኅሣሥ 3,20 18 ዓ.ም. በአስመራ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ መሠረት ኤርትራ ከምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) አባልነት በይፋ መውጣቷን አስታውቋል።

የኤርትራ መንግሥት እንዳለው ከሆነ ኢጋድ ”ሕጋዊ ሥልጣኑን እና ተልእኮውን አጥቷል” በሚል እምነት ውሳኔው ተወስዷል።

ኤርትራ ድርጅቱ ”ለአባል አገራት ስትራቴጂያዊ ጥቅሞችን አይሰጥም እንዲሁም በክልሉ መረጋጋት ለማምጣት ትርጉም ያለው ሚና መጫወት አልቻለም” ብላለች።


ድርጅቱ በ2023 ባደረገው 14ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ኤርትራ ከሁለት አስርት አመታት ከወጣችበት ድርጅት እንደገና እንድትመለስ ውሳኔ ሰጥቶ ነበር።

ሀገሪቷ በዚሁ አመት በሁሉም የአባል ሀገራት ሙሉ ድጋፍ አግኝታ በድጋሚ ወደ ድርጅቱ መመለሷን አስታውሷል።

ሀገሪቷ በድጋሚ ወደ ድርጅቱ ብትቀላቀልም ላለፉት አስራ አንድ ወራቶች ድርጅቱ ባደረጋቸው ስብሰባዎች ላይ እንዳልተሳተፈች ነው የገለጸው።

ኢጋድ በተደጋጋሚ ሀገሪቷ ድርጅቱ በሚያደርጋቸው ጉባኤዎች ላይ እንድትሳተፈፍ ተማጽኖና ውትወታዎች ቢያደርግም እንዳልተሳካለት ገልጿል።

ኢጋድ ከሀገሪቷ ጋር ሰፊ ውይይቶች ማድረግ ቢፈልግም ከኤርትራ በኩል ሰሚ አለማግኘቱን አሳውቋል።

አሁንም ለውይይት ኢጋድ በሩ ክፍት መሆኑን በመጠቆም ኤርትሪያ ለውይይት በሯን ክፍት እንድታደርግ ጠይቋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...