ኤርትራ የአውሮፓ ህብረትን ወነጀለች

Date:

የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረ መስቀል፣ የአውሮፓ ኅብረት ሀገራቸውን “ለመቅጣት”  የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤትን “እንደ መሣሪያ” እንደሚጠቀም ከሰሱ።

ሚኒስትሩ ዋና መቀመጫውን በጄኔቭ ያደረገውን የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት፣ “እየከሰመ ያለ ዓለም አቀፍ ሥርዓት ቅሪት” ሲሉ አጣጥለውታል፡፡

“ለራሳቸው የሞራል ልዕልና ያጎናጸፉ” ያሏቸው “የተወሰኑ” ልዕለ-ኃያላን፣ ለትዕዛዞቻቸው “የማይንበረከኩትን ለመቅጣት”፣ የተመድ የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤትን እንደ መሣሪያ ይጠቀማሉ ሲሉ አቶ የማነ በኤክስ ባሰፈሩት መልክት ወንጅለዋል።

አቶ የማነ የአውሮፓ ኅብረትን  የወነጀሉት መንግሥታቸው በኤርትራ ተፈጽመዋል የተባሉ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን ለመመርመር በተባበሩት መንግሥታት የሚሾሙ ባለሙያ ሥልጣን እንዲያበቃ ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ በተደረገ ማግስት  ነው። 

DW Amharic

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...