እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት ፈጽማ የአስቸኳይ ጊዜ አወጀች

Date:

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር በኢራን ላይ ‘ቀድሞ የማጥቃት’ እርምጃ መውሰዱን ሲያስታውቅ በመላዋ አገሪቱ የአደጋ ጊዜ የማስጠንቀቂያ ደውል መሰማቱ ተዘገበ።

እስራኤል ጥቃቱን ተከትሎ በመላዋ አገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አውጃለች።

እርምጃው ከኢራን በኩል ሊፈጸም የሚችል ጥቃትን ቀድሞ ለመከላከል የተወሰደ መሆኑን ገልጾ፣ ይህንን ተከትሎ ከኢራን በኩል የአጸፋ የሚሳዔል ጥቃት ሊፈጸም እንደሚችል አስጠንቅቋል።

በተጨማሪም የእስራኤል መከላከያ ኃይል ‘ተደጋጋሚ የተኩስ አቁም ጥሰት በመፈጸሙ’ በጎረቤት ደቡባዊ ሊባኖስ ውስጥ በሚገኙ የሄዝቦላህ ጥቃት መፈጸሙንም አስታውቋል።

የቢቢሲ የኢራን ቋንቋ አገልግሎት ፋርስ ዜና ወኪል በመጥቀስ እንደዘገበው በኢራን ዋና ከተማ ቴህራን ማዕከላዊ ክፍል ውስጥ በርካታ ፍንዳታዎች መሰማታቸውን ዘግቧል።

የዜና ወኪሉ ቴህራን ውስጥ የሚገኙ ሁለት አካባቢዎች በተለይ ዒላማ መሆናቸውን እና በተጨማሪም ሦስት ፍንዳታዎችን የሚያሳዩ ሦስት ፎቶዎችንም አጋርቷል።

ፍንዳታ
የምስሉ መግለጫ,በተለያዩ የቴህራን ክፍሎች ውስጥ ፍንዳታዎች ተሰተምዋል

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...