ከቀልድ በስተጀርባ ያለፈው ሕይወት

Date:

በአሜሪካ ጆርጂያ ግዛት የሚገኝ አንድ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ በተማሪዎቹ ዘንድ እጅግ በሚወደድ መምህሩ ድንገተኛ ሞት በሐዘን ተመቷል።

መምህር ጄሰን ሁግስ ለህልፈት የተዳረጉት ተማሪዎቹ በቤቱ ዙሪያ ባዘጋጁት የ’ፕራንክ’ ወይም የመጫወቻ ቀልድ ሳቢያ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ ነው።

ተማሪዎቹ በመምህሩ መኖሪያ ግቢ በሚገኙ ዛፎች ላይ የሽንት ቤት ወረቀቶችን በመበተን ጨዋታ ላይ ሳሉ፣ መምህሩ ሁኔታውን ለመመልከት ወደ ውጭ ወጥቶ ነበር።

ይሁን እንጂ በዝናብ ምክንያት በደረሰ የመንሸራተት አደጋ መሬት ላይ በወደቀበት ቅጽበት፣ ተማሪዎቹ እንዳያያቸው ለማምለጥ በፍጥነት ሲያሽከረክሩት በነበረ መኪና ተገጭቶ ሕይወቱ አልፏል።

ምንም እንኳን ፖሊስ በተማሪዎቹ ላይ የክስ ሂደት ቢጀምርም፣ የመምህሩ ባለቤትና ቤተሰቦች ግን ክሱ እንዲቋረጥ ጠይቀዋል።

መምህር ጄሰን ከልጆቹ ጋር አብሮ ለመጫወት በጉጉት ይጠብቅ እንደነበር የገለጹት ባለቤታቸው፣ ሁኔታው አሳዛኝ አደጋ እንጂ ሆን ተብሎ የተደረገ አለመሆኑን በመግለጽ ይቅርታን መርጠዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ በጡረታ ከኃላፊነታቸው ተሰናበቱ

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያንና የአዲስ አበባ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ...

አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ አዲስ መግለጫ አወጣች

ታዋቂዋ አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ ለስፖርት ወዳጆችና ለደጋፊዎቿ ወቅታዊ መረጃ...

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...