ከቻይና እና ከብራዚል ጋር ፍርደኞች ማስተላለፍ የሚያስችል አዋጅ ፀደቀ

Date:

የህዝብ እንደራሴዎች የአዋጁ እንዴት ተፈፃሚ ይሆናል? በሚል ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 5ኛ ዓመት ስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ስብሰባው፤ ኢትዮጵያ ከቻይና፣ ከብራዚልና ከደቡብ አፍሪካ መንግስታት ጋር በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችንና ፍርደኞችን ለማስተላለፍ ያደረገችው ስምምነትን የተመለከቱ 3 ረቂቅ አዋጆችን አስመልክቶ ከህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቀረቡለትን የውሳኔ ሃሳቦች መርምሮ ረቂቅ አዋጆች በመመርመር አፅድቋል፡፡

በኢትዮጵያ እና በቻይና መንግስት መካከል የተደረገው የወንጀል ጉዳዮች የጋራ የህግ ትብብር ስምምነት በተመለከተ ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ ለምክር ቤቱ በንባብ ያቀረቡት የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወ/ሮ እፀገነት መንግስቱ ፤ ሁለቱ ሃገራት ፍርደኞችን በመለዋወጥ ፍርዳቸውን በየሃገሮቻቸው እንዲጨርሱ ለማድረግ ከቻይና መንግስት ጋር የተደረገው ስምምነት የፍርደኞችን መብት ያከበረ፤ አለም አቀፍ ሂደትን መሰረት ያደረገ ውጤታማ የፍርደኞች ማስተላለፍ እንዲኖር ለማድረግ የሚያግዝ መሆን ጠቅሰዋል፡፡

የሁለቱ ሃገራት የቀደመና ዘለቅ ላለ ጊዜ የቆየው የዲፕሎማሲና የንግድ ግንኙነት ይህንን ስምምነት ለመተግበር እንደሚያግዝና ቀጣዩን የሃገራቱን ግንኑነት እንደሚያጠናክረው ታምኖበታል ብለዋል፤ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወ/ሮ እፀገነት፡፡


በስምምነቶቹ ላይ ጥያቄ ያነሱት የፓርላማ አባላት በተለይ በኢትዮጵያ በአብዛኛው ወንጀል ፈፅመው የሚገኙት የቻይና ዜጎች በህገ ወጥ የማዕድን ማውጣትና በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር መሆኑን ጠቅሰው፤ እነዚህ ከባድ ወንጀሎች የሃገራችንን ኢኮኖሚ የሚጎዱ ናቸው፡፡

ወንጀል ፈፃሚዎቹን አሳልፎ ለሃገራቸው መንግስት ለመስጠት ስንስማማ መንግስታቸው ቅጣታቸውን እንዲጨርሱ እንደሚያደርግ ምን ያህል እርግጠኞች  ነን? ስምምነቱ እኩል ተፈፃሚነት ይኖረዋል ወይ? የሚል ጥያቄ አንስተዋል፡፡

ለጥያቄው ምላሽ የሰጡት ህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዋ ወ/ሮ እፀገነት በበኩላቸው ስምምነቱ ሁለቱም ሃገራት በፍቃዳቸው ተስማምተው የሚፈጽሙት በመሆኑ አንዱ ሃገር ሌላው ሃገር ላይ ጫና የሚያሳድርገበት ምክንያት እንደሌለ አስረድተዋል፡፡

በተጨማሪም የሰዎችን ሰብዓዊ ክብራቸው ተጠብቆ በሃገራቸው ፍርዳቸውን እንዲጨርሱ እድል የሚሰጥ ስምምነት እንደሆነም ጠቅሰዋል፡፡

ምክር ቤቱ በዛሬው ስብሰባው ከተመለከታቸው ጉዳዮች መካከል የሆኑት በኢትዮጵያና  በቻይና፣ በብራዚል እንዲሁም  በደቡብ አፍሪካ መንግስታት መካከል በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችንና ፍርደኞችን የማስተላለፍ ስምምነትን የተመለከቱትን 3ቱንም አዋጆች በአባላጫ ድምፅ አጽድቋል.።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...