የመታሰቢያ ጥሪ ለአርቲስት ነፃነት ወርቅነህ

Date:

በቅርቡ በሞት የተለየን ድንቅ የጥበብ ሰው አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ተወልዶ ባደገበትና የልጅነት ትዝታዎቹ ባሉበት በደብረ ፅጌ ቅዱሥ ዑራኤል ቤተክርስቲያን ታላቅ የመታሰቢያ እና የጸሎት መርሐ-ግብር ተሰናድቷል።

የአካባቢው ወጣቶች በጋራ ባዘጋጁት በዚህ መንፈሳዊ መድረክ ላይ፤ የሻማ ማብራት ስነ-ስርዓት የሚከናወን ሲሆን ብፁሃን አባቶች፣ መምህራነ ወንጌል፣ ዘማሪያን እንዲሁም የስራ ባልደረቦቹና ቤተሰቦቹ ይታደማሉ።

የአርቲስቱ አድናቂዎች፣ የጥበብ ቤተሰቦችና ወዳጆች ሁሉ በዚህ የክብር መርሐ-ግብር ላይ በመገኘት አብራችሁን እንድትሆኑ የዑራኤል አካባቢ ወጣቶች ጥሪያቸውን ያቀርባሉ።

መርሐ-ግብሩ የሚከናወንበት፦

  • ቀን፦ አርብ ጥር 15 ቀን 2018 ዓ.ም
  • ሰዓት፦ ከቀኑ 10:00 ጀምሮ
  • ቦታ፦ ደብረ ፅጌ ቅዱሥ ዑራኤል ቤተክርስቲያን (ዑራኤል)

ለወንድማችን ነፃነት ወርቅነህ የዘላለም እረፍትን እንመኛለን።

ነፍስ ይማር!

ለወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት መረጃውን ያድርሱ።

Via የደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል አካባቢ ወጣቶች መንፈሳዊ የአገልግሎት ማህበር ነን

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...