ከ17 የአፍሪካ ሀገራት በሚገቡ ዜጎች ላይ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ምርመራ እየተደረገ ነው

Date:

ከኬንያ፣ ዩጋንዳ እና ናይጀሪያን ጨምሮበአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በኩል ወደ ኢትዮጵያ በሚገቡ 17 የአፍሪካ ሀገራት ዜጎች ላይ የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ ምርመራ እያደረገ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል።

እነዚህ ሀገራት የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽኝ ስርጭትና ስጋቱ ያየለባቸው መሆናቸውንታሳቢ ያደረገ እርምጃ ስለመሆኑ አራዳ ሰምቷል።

በዚህ ዝርዝር ውስጥ ከተካተቱት መካከል የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ፣ ብሩንዲ፣ ላይቤሪያ እና ጋና ይገኙበታል።

ኢንስቲትዩቱ ከሚመለከታቸው ሌሎች የጤና ተቋማት ጋር በመሆን በኢትዮጵያ አየርመንገድ በኩል የሚገቡትን ጨምሮ በሀገሪቱ የመግቢያና የመውጫ ድንበሮች ላይ የቅድመ ምርመራ ሥራ እያከናወንኩ ነው ብሏል።

በሽታው ከተከሰተባቸው ጎረቤት ሀገራት ጋርም በችግሩ ዙሪያ የጋራ ምክክር በየወቅቱ እየተደረገ እንደሚገኝ ነው ያመላከተው።

በሀገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችና የውጭ ስደተኞች በሚገኙባቸውመጠለያ ጣቢያዎች ላይ ወረርሽኙ እንዳይከሰት ክትትል እየተደረገ መሆኑን አራዳ የሰማ ሲሆን እስካሁን በእነዚህ ቦታዎች በቫይረሱ የተያዘ ሰው አልተገኘም።

በሽታው ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ ከታወቀ ወዲህ 1 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑዜጎች የቅድመ ምርመራ ሥራ መስራቱ ተገልጿል።

በኢትዮጵያ በሰባት ክልሎች በቫይረሱ የተያዙ ዜጎች መገኘታቸው የተገለፀ ሲሆን
አንድ ህፃን በሞያሌ ከተማ በዚሁ ችግር ህይወቱን ማጣቱን የኢንስቲትዩቱ መረጃ ያሳያል።

@Arada_Fm

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...