ስፔናዊው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ከማንችስተር ዩኒቨርሲቲ የክብር ዲግሪ እንደተሰጣቸው ተገልጿል።
አሰልጣኙ ያገኙት የክብር ዲግሪ ለማንችስተር ከተማ በስፖርቱ እንዲሁም ከሜዳ ውጪ ላደረጉት አስተዋጽኦ እውቅና እንደሆነ ተነግሯል።
በሽልማቱ ወቅት አስተያየታቸውን የሰጡት ፔፕ ጋርዲዮላ ” ማንችስተር ለእኔ ልዩ ስፍራ አለው ዘጠኝ አመታት አሳልፌያለሁ አሁን እንደ ቤቴ ነው “ብለዋል።
አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በንግግራቸው ወቅት ስለ ጋዛ ያነሱ ሲሆን “ በጋዛ እያየን ያለነው ነገር በጣም ያማል ሙሉ አካሌን ይሰማኛል ” ሲሉ ተናግረዋል።
ፔፕ ጋርዲዮላ አክለውም ” በሺዎች የሚቆጠሩ ህፃናት እናቶች እና አባቶች እየተሰቃዩ ነው “ ሲሉ ከጋዛ በተጨማሪም በዩክሬን እና ሱዳን ጉዳት ለደረሰባቸው ንፁሃን ድጋፋቸውን ሰጥተዋል።
